የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ አውስትራሊያ የመጀመሪያ ዙር ክትባት 90 ፐርሰንት ዒላማዋን አለፈች

*** ቪክቶሪያ ውስጥ 1,115 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ዘጠኝ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

COVID-19 update

Higher vaccination rate in the country would mean greater freedoms. Source: AAP

  • የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ቁጥር 90 ፐርሰንት አለፈ።
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የፌዴራል መንግሥቱ በቪክቶሪያ ወረርሽኝ ድንጋጌዎች ጣልቃ እንደማይገባ አስታወቁ። 
  • የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አናስታዥያ ፓለሼይ የ12 ክፍል መልቀቂያ የጨረሱ ተማሪዎችን ዓመታዊ ፓርቲ እንደማይሰርዙ ገልጠው፤ ሆኖም ምንጩ ያልታወቀ ቫይረስ ከተከሰተ ግና ብርቱ ውሳኔ ለማሳለፍ እንደማያመነቱ አሳሰቡ።
  • ታዝማኒያ ዕድሜያቸው ከ 16-24 ያሉና ክትባት የተከተቡ በቡድን የመሰብሰብና የዳንስ ፌስቲቫሎች ላይ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎችን አስመልክቶ የገደቦች ክለሳ እያደረገች ነው።
  • የምዕራብ አውስትራሊያ ክትባት ኮሚሽነር ክሪስ ዳውሰን የክትባት ደረጃው ዝቅተኛ የሆነባቸው ነባር ዜጎች መኖሪያ ሥፍራ ላሉ የማኅበረሰብ አረጋውያን በግል ተማፅኖ አቀረቡ። 
  • ከኖቬምበር 15 ጀምሮ ሲድኒ ውስጥ በብርቱ አስፈላጊ ያልሆኑ የቀዶ ሕክምና ግልጋሎቶች በሙሉ አቅም ይሰጣል። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,115 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ዘጠኝ ሕይወታቸውን አጥተዋል።  
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 286 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታወቀች። 
ኩዊንስላንድ ውስት ሁለት ሰዎች በቫይረስ ሲያዙ፤ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 15 ነዋሪዎች ተጠቅተዋል። 

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


NSW 
ACT 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 
ACT 
 


Share

Published

Updated

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service