- ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ሶስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት ከኖቬምበር 8 ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀምር አስታወቁ
- ቪክቶሪያ በወረርሽኝ ሳቢያ ከፍተኛ ዕለታዊ የሟቾች ቁጥር አስመዘገበች
- ኩዊንስላንድ በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ሳይከተቡ የቀሩ 150 የፖሊስ ሠራዊት አባላትን ከሥራቸው ተገልለው እንዲቆዩ ወሰነች
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,923 ነዋሪዎች በ25 ዕለታዊ የኮቪድ ሟቾች ቁጥርን አስመዘገበ ተጠቁ፤ 25 ዕለታዊ የኮቪድ ሟቾች ቁጥርን አስመዘገበች።
ይህ የሆነውም ክለ አገሪቱ በነገው ዕለት ተጨማሪ ገደቦች ለማንሳት በመሰናዶ ላይ ሳለች ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ለሟች ቤተሰቦች የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን በመግለጽ “ይህ የወረርሽኙን አስከፊ ዕውነታ ልብ የሚያሰኝ አስደማሚ ሁነት ነው" ብለዋል።
የቪክቶሪያ ጤና ዲፓርትመንት ከኮቪድ-19 ክትባት ራሳቸውን ያገለሉ ሰዎች የአውስትራሊያ ክትባት ምዝገባ ማረጋገጫቸውን የሚያቀርቡብት ጊዜ አሁን መሆኑን አሳሰበ።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 293 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
ከዳርሊንግኸርስት የአካል ማጠንከሪያ ሥፍራ ጋር በተያያዘ 15 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።
ከኦክቶበር 18 እስከ 23 ወይም 25 ባሉት ጊዜያት ውስጥ የአካል ማጠንከሪያ ሥፍራው ላይ የተገኙ ሰዎች ምርመራ እንዲያካሂዱና ከቫይረስ ነፃ ለመሆናቸው ማረጋገጫ እስኪያገኙም ድረስ ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
የደንበኞች ግልጋሎት ሚኒስትር ቪክቶር ዶሚኒሎ ከዓርብ ጀምሮ ተጋላጭ ሥፍራዎች ላይ የተገኙ ሰዎች በሰርቪስ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ኧፕ አማካይነት ማሳሰቢያ እንደሚደርሳቸው ገለጡ።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
ኩዊንስላንድ
ኦክቶበር 4 ቀነ ገደብ መከተብ ሲገባቸው ያልተከተቡ 150 ያህል የኩዊንስላንድ ፖሊስ ሠራዊት አባላት ከሥራቸው ተገልለው እንዲቆዩ ተወሰነ።
ኩዊንስላንድ ውስጥ በዛሬው ዕለት አንድም ግለሰብ በቫይረስ አልተያዘም።
የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ አሁኑኑ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ከኖቬምበር 8 ጀምሮ የመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር ማጠናከሪያ ከትባቶች በሁሉም የአውስትራሊያ መድኃኒት ቤቶች ይገኛል።
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ስምንት ነዋሪዎች በቫይረስ ተያዙ።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ሶስት አራተኛ አውስትራሊያውያን ሙሉ ክትባት የተከተቡ መሆናቸውን ገለጡ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

