የኮቪድ-19 የተሻሻለ መረጃ ፡ በኒው ሳውዝ ዊልስ የሟቾች ቁጥር እንደሚጨምር የሚጠብቅ ሲሆን በቪክቶሪያም ከፍተኛ የሚባልባት ደረጃ ለመድረስ ተቃርቧል

*** በኒው ሳውዝ ዌልስ 29,504 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል ። በቪክቶሪያ 22,429 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የስድስት ሰዎች ህይወትም አልፏል ።

Victorian Chief Health Officer Brett Sutton addresses the media during a press conference in Melbourne.

Victorian Chief Health Officer Brett Sutton addresses the media during a press conference in Melbourne. Source: AAP

    • በመጪዎቹ ቀናት በኒው ሳውዝ ዌልስ በኮቪድ- 19ሳቢያ የሟቾች ቁጥር እንደሚጨምር የሚጠበቅ ሲሆን ፤ ይህም የሚሆነው በማህበረሰብ መካከል በሚሰራጭ ቫይረስ አማካኝነት መሆኑን ከፍተኛ የጤና ኦፊሰሯ ኬሪ ቻንት አስጠንቅቀዋል ።
    • በኒው ሳውዝ ዌልስ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ 17 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ፤ በተያያዥም በሆስፒታል እና ልዩ እንክብካቤ የሚስፈልጋቸው ሰዎች በሚታከሙበት ክፍል የሚቆዩ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተገልጿል ።
    • ዶ / ር ቻንት እንደተናገሩት “ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባትን በመውሰድ ፤ መከላከያን ከፍ በማድረግ ኦሚኮርንን መከላከል ግድ ይላል ፤ በሪፖርታቸውም አያይዘው እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ቀናት በግል የደም መስጫ ተቋም ከተሰበሰቡት ናሙናዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት የኦሚኮርን ቫርያንት ናቸው ።
    • የቪክቶሪያ ከፍተኛ የጤና ኦፊሰር ብሬት ሰተን ፤ ምንም እንኳ በማህበረሰቡ ውስጥ የተዛመተው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቫይረስ ስርጭት ሪፖርት ባይደረግም ፤ ከተማዋ በቅርቡ ሰርጭቱ “ ከፍተኛ ” ደረጃ የሚባልበት ላይ እንደምትደርስ ተናግረዋል ።
    • ከኩዊንስላንድ የተገኙት የቁጥር መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ፤ አንድ ያልተከተበ ሰው ሶስቱንም ክትባቶች ከወሰዱት ጋር ሲነጻጸር ፤ ከፍተኛ እንክብካቤ የሚያሻቸው ህሙማን ክፍል ውስጥ የመቆየት እደሉ በ24 እጥፍ ከፍ ያለ ነው ።
    • የአውስትራሊያ ተጠቃሚዎች ተቆጣጣሪ እንዳለው የፈጣን መመርመሪ መሳሪያዎቹ ዋጋ በየጊዜው መናር አሳሳቢ መሆኑን ነው ።
    • የአውስትራሊያ ተጠቃሚዎች ተቆጣጣሪ ከ 1,800 በላይ አሀዛዊ ሪፖርቶችን የተነተነ ሲሆን ፤ የዋጋ መጨመር የታየው ካለፈው ዲሴምበር 25 ጀምሮ ሲሆን ፤ በአሁን ሰአትም ከ 150 በላይ ሪፖርቶች በየቀኑ ይወጣሉ ።
    • ቪክቶሪያ ክትባትን ለማበረታታት 1.2 ሚሊዮን ዶላር ለመድበለ ባህል የማህበረሰብ አባላት የመደበች ሲሆን ፤ ይህውም በስምንት የማህበረሰብ ድርጅቶች አማካኝነት የቋንቋ እርዳታን ለሚሹ ፤ በገበያ ማእከላት እና የክትባት ጣቢያዎች ክትባቱን ለማዳረስ የሚወል ይሆናል ።
    • የፌደራል መንግስት በጊዜያዊነት የሚያገለግል የልዩ ሀኪሞች ቴሌ ሄልዝ በስልክ እና ቪዲዮ አገልግሎት የሚያስተዋውቅ ሲሆን ፤ ይህውም የመጀመሪያ እና ውስብስብ ልዩ የስልክ ህክምናን ፣ ረጅም የቤተሰብ ሀኪም ማማከርን የሚያጠቃልል እና እስከ ጁን 30 የሚዘልቅ ነው ።
    • ኮቫክ ( COVAX )  የተባለው አለማቀፍ ድርጅት ክትባትን በመጋራት ዙሪያ አንድ ቢሊዮን ክትባቶችን ያዳረስ ቢሆንም ፤ እስከአሁንም ድረስ 40 በመቶ የሚሆነው የአለማችን ህብረተሰብ አልተከተበም ።
    የፈጣን ምርመራን ቅጽ ያዘጋጁ ክፍላት ሃገራት ዝርዝር ፦

    የኮቪድ - 19 ስታትስቲክስ

  • በኒው ሳውዝ ዌልስ 29,504 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል ። በቪክቶሪያ 22, 429 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የስድስት ሰዎች ህይወትም አልፏል ።

  • በኩዊንስላንድ 15,122 ስዎች ሲያዙ የ 7 ስዎች ህይወት አልፏል ። በታዝማንያ 1037 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ።

  •  በአሁን ሰአት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ላይ እየተሰጠ ያለውን ምላሽ በተመለከተ በቋንቋዎ መረጃን ካሹ የሚከትለውን ሊንክ ይጫኑ here.


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር ፤

ጉዞ

የአለማቀፍ ጉዞን በተመለከተ መረጃዎችን እና የ ኮቪድ-19 የጉዞ መረጃዎችን በቋንቋዎ ያግኙ

የአለማቀፍ ጉዞን በተመለከተ መረጃዎችን Information for international travellers እና የ ኮቪድ-19 የጉዞ መረጃዎችን በቋንቋዎ ያግኙ in language

የገንዘብ እርዳታ

በየክፍላት ሀገሩ ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ከ 70 እና 80 በላይ ከሆነ ጀምሮ የክፍለ ሀገሮች የኮቪድ-19 የአደጋ ጊዜ ክፍያ ህጎች ተለውጠዋል።:

 



በኒው ሳውዝ ሄልዝ መድብለባህል የጤና ክህለ ተግባቦት አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ ፦


የየክፍላተ ሀገራቱ እና ግዛቶች የመመርመሪያ ክሊኒኮች ዝርዝር ፦

NSW 
ACT 

Share

Published

Updated

Presented by Martha Tsegaw

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service