የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ከዛሬ 6pm ጀምሮ ሊዝሞር እና አልበሪ ላይ ለሰባት ቀናት የሚቆይ የኮሮናቫይረስ ገደብ ተጣለ

*** ቪክቶሪያ የተወሰኑ ገደቦችን አላላች

COVID-19 update

The regional LGAs of Lismore and Albury will go into a seven-day lockdown from 6pm tonight, 16 September 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 12 የአሳሳቢ አካባቢ መንግሥታት ክፍለ ከተሞች ከተጣለባቸው ገደብ ወጡ
  • ቪክቶሪያ የተወሰኑ ገደቦችን አላላች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የኮቪድ-19 ድጎማዎችን ጨመረች
  • ኩዊንስላንድ አንድ ወሸባ ውስጥ ያለ ግለሰብ በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,351 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ሕይወታቸውን ካጡት 12 ሰዎች ውስጥ 10ሩ ያልተከተቡ ናቸው።

በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ሳቢያ ከዛሬ 6pm ጀምሮ ሊዝሞር እና አልበሪ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ገደብ ተጥሎባቸዋል።  

ከዛሬ 1 pm ጀምሮ Bega Valley, Blayney, Bogan, Cabonne, Dungog, Forbes, Muswellbrook, Narrabri, Parkes, Singleton Snowy Monaro እና Upper Hunter Shire ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች ይረግባሉ

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 514 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። በጠቅላላው 4,370 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል።

ቪክቶሪያ ውስጥ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥር 70 ፐርሰንት ይደርሳል። ሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው ያሉ የተወሰኑ ገደቦች ከዓርብ እኩለ ለሊት ጀምሮ ይረግባሉ some restrictions will ease 

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች በቡድን ከአምስት ሳይበልጡ ከቤታቸው ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ። ከትባት ያልተከተቡ ወይም የመጀመሪያ ዙር ክትባት ብቻ የተከተቡ ሰዎች ከሁለት በላይ መሰባሰብ አይፈቀድላቸውም። ለሸመታና አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ነዋሪዎች ቀደም ሲል ከነበረው የ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ገደብ አልፈው ከቤታቸው እስከ 10 ኪሎ ሜትር ርቀው መሔድ  ይችላሉ።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

15 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል።  

የጋራ ብልጽና እና የአውስትራሊያ ካፒታል መንግሥት ለቱሪዝም፣ የመኝታ ግልጋሎት ሰጪዎች፣ ሥነ ጥበብ፣ ኩነቶችና መስተንግዶ ዘርፎች የኮቪድ-19 የንግድ ድጎማዎችን ጨምረው ለመስጠት ተስማምተዋል። ድጎማ ለማግኘት ማመልከት ካሹና ተጨማሪ መረጃን ከፈለጉ ይህን ይጫኑ here

የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን ያሟሉ እንደሁ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccination.                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የሰሜናዊ ቴሪቶሪ በወርኃ ኖቬምበር መጀመሪያ 80 ፐርሰንት ያህል ነዋሪዎችን ሙሉ ክትባት ለመከተብ አልሟል።

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 


3 min read

Published

Updated

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now