የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ የአገር ውስጥ ተጓዦች በክፍለ አገር መንግሥታት ክሊኒኮች ከክፍያ ነፃ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ ይችላሉ

*** በሚቀጥለው ዓመት ከጃኑዋሪ 17 ጀምሮ የኒውዝላንድ ዜጎችና ሌሎችም የጉዞ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ መንገደኞች ወደ ኒውዝላንድ መጓዝ ይችላሉ።

COVID-19 update

A woman waits to receive a COVID-19 test in the eastern suburbs of Sydney Tuesday, Sept. 14, 2021. Source: AAP

የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት የአገር ውስጥ ተጓዦች በክፍለ አገር መንግሥታት ክሊኒኮች ለሚያደርጉት የኮቪድ-19 ምርመራ ክፍያ መፈጸም አንደማይጠበቅባቸው አስታወቁ። ቀደም ሲል የአገር ውስጥ መንገደኞች ለአንድ ምርመራ $150 መክፈል ይኖርባቸው ወይም አይኖርባቸው እንደሁ ብዥታ ፈጥሮ ነበር። 

ኩዊንስላንድ፣ ምዕራብ አውስትራሊያና ደቡብ አውስትራሊያ መንገደኞች ከግዛታቸው ከመዝለቃቸው በፊት 72 ሰዓታት ቀደም ብለው አፍንጫና ጉሮሮን ያካተተ የቫይረስ ምርመራን PCR ውጤት እንዲያቀርቡ ግድ ይላሉ።

በሚቀጥለው ዓመት ከጃኑዋሪ 17 ጀምሮ የኒውዝላንድ ዜጎችና ሌሎችም የጉዞ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ መንገደኞች ወደ ኒውዝላንድ መጓዝ ይችላሉ። የሆቴል ወሸባ መግባትም አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ለሰባት ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ መግባት ይጠበቅባቸዋል።

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,196 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 248 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታወቀች። 

ኖርዘን ቴሪቶሪ ውስጥ 11 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ኩዊንስላንድ ውስጥ በቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ አልተመዘገበም።

በቫይረስ ተይዘዋል።

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

Find out what you can and can't do in your state or territory

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


 

 


1 min read

Published

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now