- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዳቦ ሪጅን ገደብ ተጣለበት
- ቪክቶሪያ ውስጥ አምስት የቫይረስ ምንጮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው
- ኬይንስ ላይ የተጣለው ገደብ ተነሳ
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 20 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። አምስቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። ስድስቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ሜልበርን ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እስከ ሐሙስ ኦገስት 19 መራዘሙን አስታወቁ።
በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination centres.
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 344 ሰዎች በቫይረስ የተያዙባት ሲሆን 65 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። አንድ ዕድሜያቸው በ90ዎቹ ያሉና አንድ በ30ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ግለሰብ በኮቪድ-19 ተጠቅተው ሕይወታቸው አልፏል። ሁለቱም ክትባት ያልተከተቡ ነበሩ።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዳቦ ሪጂን ላይ ከዛሬ ረቡዕ ኦገስት 11 ከቀትር በኋላ 1pm ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ገደብ ተጥሏል። ለገደቡ መጣል አስባብ የሆነውም ሁለት ግለሰቦች በቫይረስ ተጠቅተው በመገኘታቸው ነው።
ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ኬሪ ቻንት እንደገለጡት በፅኑዕ ህሙማን ክፍል በመታከም ካሉት 62 ሰዎች ውስጥ 57ቱ ያልተከተቡ ሲሆን አምስቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ ናቸው።
በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.
ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ ውስጥ አራት ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ሁሉም ቀደም ሲል ቫይረሱ ተዛምቶባቸው ያሉ ሥፍራዎች ነዋሪዎችና ወሸባ ገብተው የሚገኙ ናቸው።
ኬይንስ እና ያራባህ ላይ ተጥለው የነበሩት ገደቦች ከዛሬ 4 pm ጀምሮ ይረግባሉ፤ የተወሰኑ ገደቦች ጸንተው ይቀጥላሉ restrictions remain in place.
ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ጃኔት ያንግ ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸውና ዕድሜያቸው ከ12-15 ያሉ ልጆች ለክትባት እንዲመዘገቡ አሳስበዋል።
የክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccination appointment.
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

