የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኳንታስ ዓለም አቀፍ በረራ ሊጀምር ነው

*** ከኖቬምበር 1 ጀምሮ ሙሉ ክትባት ተከትበው ከባሕር ማዶ ወደ ቪክቶሪያ የሚመጡ አውስትራሊያውያን ወሸባ እንዳይገቡ ተወሰነ።

COVID-19 update

Melbourne has emerged from the world's longest lockdown, and as vaccination rates continue to rise. Source: AAP

  • የቪክቶሪያ ገደብ በላላበት ዕለት 16 ሰዎች በኮቪድ-19 ሕይወታቸው አለፈ፤  2,189 በቫይረስ ተጠቁ።
  • ኳንታስ የዓለም አቀፍ በረራ ዕቅዱን አሻሻለ
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን መንግሥት ከሲንጋፖር ጋር የመንገድኞች በረራ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረቡን ጠቆሙ

 ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ ውስጥ 2,189 በኮቪድ-19 ተጠቁ፤ 16 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ሜልበርን በዓለም ረጅም ከተባለው የኮሮናቫይረስ ገደብ ቆይታ ተላቅቃለች።

ሙሉ ክትባት የተከተቡ የከፍለ አገሪቱ ነዋሪዎች ቁጥር ቀደም ብሎ ታስቦ ከነበረው ኖቬምበር 5 በአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ኦክቶበር 30 ላይ 80 ፐርሰንት ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል። 

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ከኖቬምበር 1 ጀምሮ ሙሉ ክትባት ተከትበው ከባሕር ማዶ ወደ ቪክቶሪያ የሚመጡ አውስትራሊያውያን ወሸባ እንዳይገቡ መወሰኑን አስታወቀዋል።  

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

 ኒው ሳውዝ ዌይልስ 345 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

ኳንታስ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሠራተኞቹን ወደ ሥራ መልሶ የዓለም አቀፍ በረራውን ለመጨመር ማቀዱን ባስታወቀበት በዛሬው ዕለት፤ ሲድኒ አውሮፕላን ማረፊያ የተገኙት እንደራሴ ዶሚኒክ ፔሮቴይ ኒው ሳውዝ ዌይልስ "የመልሶ መቋቋም ማኮብኮቢያ" ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል። 

በሥፍራው ተገኝተው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንም በበኩላቸው አውስትራሊያውያን ወደ ሲንጋፖር መጓዝ እንዲችሉ በመጪው ሳምንት ከስምምነት ላይ ለመድረስ የመቋጫ ንግግር ላይ መኮኑን አመላክተዋል።  

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 13 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆነ 84 ፐርሰንት ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ተከትበዋል። 

የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ አሁኑኑ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም በቫይረስ የተጠቃ ሰው አልተመዘገበም፤ ይሁንና የሎጋን ከትባት መጠን አሳሳቢ ሆኗል። በነገው ዕለት በ100 የትምህርት ቤት ቅጥር ግቢዎች ውስጥ መጠነ ሰፊ 'የልዕለ ቅዳሜ' ክትባት ይካሄዳል።

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 

 

 

 


3 min read

Published

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now