- የክፍለ አገራት መሪዎች በትናንትናው ዕለት በ ‘close contact’ ትርጓሜ በትናንትናው ዕለት ከስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤ በኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያ፣ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪና ኩዊንስላንድ ከዕኩለ ለሊት ጀምሮ ግብር ላይ ውሏል
- ታዝማኒያ አዲሱን የ'ቅርብ ንኪኪ' ትርጓሜ ከጃኑዋሪ 1 ጀምሮ ግብር ላይ የምታውል ሲሆን፤ ምዕራብ አውስትራሊያና ኖርዘርን ቴሪቶሪ በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ መች ግብር ላይ እንደሚያውሉት ያስታውቃሉ። ደቡብ አውስትራሊያ አዲሱን ድንጋጌ ውድቅ አድርጋለች።
- በአዲሱ ትርጓሜ መሠረት 'የቅርብ ንኪኪ' ማለት በተለየ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር፤ በአንድ ቤት ነዋሪ ከሆኑ ግለሰቦች ውስጥ አንዱ በኮቪድ-19 መያዙ ከተረጋገጠ ቤተኛ ጋር፣ ከቤት ውጪ ባሉ 'መኖሪያ ቤት መሰል' ወይም የክብካቤ ተቋም ውስጥ ከአራት ሰዓታት በላይ አብሮ ያሳለፈ ግለሰብ ነው
- ይህንኑ የትናንት የጋራ ስምምነት አዘል ትርጓሜ ግና የደቡብ አውስትራሊያ ዋና የሕዝብ ጤና መኮንን ውድቅ በማድረግ፤ የቅርብ ንኪኪ ማለት ማንኛውም በቫይረስ ከተጠቃ ግለሰብ ጋር ከ15 ደቂቃ በላይ ጊዜን ያሳለፈ ግለሰብ ማለት እንደሆነ ገልጠዋል
- በአብዛኛዎቹ ክፍለ አገራት የኮቪድ-19 ተጠቂዎችና የቅርብ ንኪኪዎች ለሰባት ቀናት ራሳቸውን እንዲያገልሉና በስድስተኛው ቀን ፈጣን ምርመራ እንዲያካሂዱ የሚያደርጉ ሲሆን፤ ደቡብ አውስትራሊያ ግና ራስን አግልሎ የመቆያ ጊዜ 10 ቀናት እንዲሆኑ ወስናለች
- ታዝማኒያ ከጃኑዋሪ 1 ጀምሮ ወደ ግዛቷ በሚዘልቁ መንገደኞች ላይ ጥላ የነበረውን የPCR ምርመራ ድንጋጌ አንስታለች
- ደቡብ አውስራሊያ ውስጥ ገና ሁለት ዓመት ሳይሞላው በኮቪድ 19 ተጠቅቶ ለሕልፈት ሕይወት የበቃው ሕፃን አሟሟት ምርመራ ውጤት እስካሁን ይፋ አልሆነም
- ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ያለ የአውስትራሊያ ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ተከታቢዎች ደረጃ 90 ፐርሰንት ደረሰ
- ፈጣን ምርመራ ማካሔጃ RAT ዋጋ አሻቅቧል፤ አንድ የሲድኒ መድኃኒት ቤት አንድ ነጠላ መመርመሪያን በ$25 እየሸጠ ነው
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 21,151 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የስድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ቪክቶሪያ ውስጥ 5,919 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኩዊንስላንድ 3,118፣ ታዝማኒያ 137 ሰዎች ተጠቅቶባቸዋል።
ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
Find out what you can and can't do in your state or territory
ጉዞ
Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤ Getting help during Covid-19 from Services Australia in language

