- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞች የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራ እንደምታካሂድ አስታወቀች
- ቪክቶሪያ ከዕኩለ ለሊት በኋላ የተወሰኑ ገደቦቿን ታረግባለች
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ የአረጋውያን መጠወሪያ ክትባት ግዴታ ሆነ
- ኩዊንስላንድ አንድ ወሸባ ያለ ሰው በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,284 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ሕይወታቸውን ካጡት 12 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ወንዶች ዕድሜያቸው 20ዎቹ ውስጥ የነበረ ናቸው። ሶስቱ የዳቦ አረጋውያውያን መጠወሪያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን ሰባቱ አልተከተቡም።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን በTGA ተቀባይነት ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዓለም አቀፍ መንገደኞች ለሰባት ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ እንዲገቡ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቁ። የመነሻ ሙከራው የሚከናወነው በ175 መንገደኞች ላይ ሲሆን በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ይጀመራል።
ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 510 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።
ከዛሬ እኩለ ለሊት አንስቶ ክትባት ያልተከተቡ ወይም የመጀመሪያ ዙር ብቻ የተከተቡ ነዋሪዎች አንድ ከመኖሪያቸው ውጪ ከሆነ ግለሰብ ጋር የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ሽርሽር መሄድ ይችላሉ። ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ከሁለት መኖሪያ ቤቶች ልጆቻቸው ሳይቆጠሩ እስከ አምስት ሆነው በቡድን የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ሽርሽር መሄድ ይፈቀድላቸዋል።
ከገደቦች መውጫንና እስከ ኖቬምበር ተጥለው የሚቆዩ የገደብ ዓይነቶችን የሚያመላክተውን ፍኖተ ካርታ መንግሥት እሑድ ሴፕቴምበር 19 ይፋ ያደርጋል።
አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
30 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል።
ከዛሬ ጀምሮ ክትባት ያልተከተቡ የአረጋውያን መጠወሪያ ሠራተኞች የመጀመሪያ የኮቪድ-19 ክትባት እስካልተከተቡ ድረስ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዳይመለሱ የተደነገገው ድንጋጌ ግብር ላይ ውሏል።
የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን ያሟሉ እንደሁ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccination.
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ታዝማኒያ ከሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለሚመጡ መንገደኞች የ30 ቀናት የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራ ታደርጋለች።
- የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤NSW Travel & transport and QuarantineVIC Travel permit, Overseas travellers and QuarantineACT Transport and QuarantineNT Travel and QuarantineQLD Travel and QuarantineSA Travel and QuarantineTAS Travel and QuarantineWA Travel and Quarantineወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤NSW Victoria Queensland South Australia ACT Western Australia TasmaniaNorthern Territory
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤NSW Victoria Queensland South Australia ACT Western Australia Tasmania
Northern Territory

