- የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፅኑዕ ህሙማን ክብካቤ ክፍሎች ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ህሙማን ያልተከተቡ ናቸው
- ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረስ የተያዙ ሰዎች በማኅበረሰብ ተጋቦት ነው
- በኩዊንስላንድ የክትባት ፕሮግራም በላይ የመድኅኒት ቤቶች ተሳታፊ ሆኑ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 292 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘውባታል፤ 48 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ነው። አንዲት ዕድሜያቸው በ60ዎቹ ውስጥ ያለ የደቡብ ምዕራብ ሲድኒ ነዋሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ቫይረሱ በብዛት በተዛመተበት ካንተርበሪ - ባንክስታውን አካባቢ የሕዝብ ጤና ድንጋጌዎች ጸንተው እንዲከበሩ የፖሊስ ኃይል እንዲጨምር ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ኬሪ ቻንት ከ50 ፅኑዕ ህሙማን ውስጥ 44ቱ ያልተከተቡ ሲሆን የተቀሩት የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ መሆናቸውን ገልጠዋል።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት ማንኛውም ነዋሪ ክትባት እንዲከተብ ጥሪ እያቀረቡ ነው። የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ትናንት ኦገስት 5 የተገለጡትን ሁለት በቫይረስ የተጠቁትን ጨምሮ በዛሬው ዕለት ስድስት ሰዎች በቫተስ መያዛቸውን ገልጣለች።
ሁሉም ስድስቱ ተጠቂዎች የተያዙት በዴልታ ሲሆን ወሸባ ገብተው የነበሩ አይደሉም።
በትናንትናው ዕለት ለተጣለው ገደብ አስባብ የሆነው በሆብሰንስ ቤይ እና ማሪቢኖንግ ተከስቶ የተዛመተ ወረርሽኝ ነው።
ቫይረሱ የተሰራጨባቸውን ሥፍራዎች ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of exposure sites.
ኩዊንስላንድ
ኩዊንስላንድ በዛሬው ዕለት10 ሰዎች በቫይረስ መያዛቸውን ገልጣለች። ሁሉም ገደብ ከተጣለባቸው አካባቢዎች ናቸው።
ከ330 በላይ የማሕበረሰብ መድኃኒት ቤቶች የኮቪድ 19 ክትባቶችን ለኩዊንስላንድ ነዋሪች እየሰጡ ነው COVID-19 vaccinations
የኩዊንስላንድ ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ጃኔት ያንግ በደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ላይ ተጥሎ ያለውን ገደብ እሑድ ኦገስት 8 ይነሳል ብሎ ለማለት ጊዜው ገና መሆኑን ተናግረዋል።
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

