- የቤተሰብ ስብስቦች ለኒው ሳውዝ ዌይልስ ቫይረስ መዛመት አንዱ ቁልፍ ምክንያት ሆኖ አለ
- ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው ያሉትን ገደቦች ለማንሳት ገና ከውሳኔ ላይ አልተደረሰም
- ደቡብ አውስትራሊያ ገደቦቿን እንደምታነሳ አስታወቀች
- ኩዊንስላንድ አንድ በቫይረስ የተጠቃ ሰው ከሲድኒ በመዝለቁ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ናት
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 145 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች። ፌርፊልድ ውስጥ የቫይረሱ መዛመት ቀንሷል። የፖሊስ ኮሚሽነር ማይክ ፉለር ሲድኒ ውስጥ ገደቦች ተጥለው ሳለ የተቃውሞ ሰልፍ የሚያደርግ ማንኛውም ግለሰብ ለእሥራት እንደሚዳረግ አስታወቁ።
በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ የአካባቢ ፋርማሲዎች ዕድሜያቸው ከ60 በላይ ለሆኑ የአስትራዜኔካ ክትባትን እንደሚከትቡና የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባት እጥረት ያለ መሆኑን የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዋና የጤና መኮንን ዶ/ር ኬሪ ቻንት ገለጡ።
ዶ/ር ቻንት የማኅበረሰብ አባላት በሙሉ እንዲከተቡ አሳስበዋል። የክትባት መስጫ ፋርማሲዎችን ለማወቅ ከፈለጉ ይህን ይጫኑ list of pharmacies.
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 11 በቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን አስመዘገበች። ሁሉም በዴልታ ቫይረስ የተጠቁና ወሸባ ውስጥ ያሉ ናቸው። በጠቅላላው በቫይረስ ተይዘው ያሉ ሰዎች ቁጥር 190 ነው።
ለአምስተኛ ጊዜ የተጣለው ገደብ ማብቂያ ማክሰኞ ምሽት 11:59 pm ጁላይ 27 ቢሆንም፤ ባለስልጣናት ግና "ከውሳኔ ላይ ገና አልተደረሰም” እያሉ ነው።
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- በደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ የፊት ጭምብል ማጥለቅ ድንጋጌ ፀንቶ አለ። ቫይረሱ ተዛምቶ ያለባቸውን ሥፍራዎች እዚህ ይመልከቱ list of exposures sites.
- ደቡብ አውስትራሊያ የጣለችውን ገደብ ረቡዕ 12:01 am ለማንሳት ከውሳኔ ላይ ደርሳለች፤ ሆኖም የተወሰኑ ገድቦች ፀንተው ይቀጥላሉ።
- በፌዴራል የጤና ዲፓርትመንት መግለጫ መሠረት አውስትራሊያ ውስጥ 2117 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘው ይገኛሉ።
የኮቪድ-19 አፈ ታሪክ፤
ጤናማ ወጣቶች በኮቪድ-19 አይጠቁም። ቫይረሱ የሚያጠቃውና የሚገድለው በዕድሜ የገፉና የታመሙን ብቻ ነው።
የኮቪድ-19 መዘርዝረ ጭብጥ፤
ቫይረሱ ፅኑ ሕመም ያለባቸው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ብርቱ ተፅዕኖዎች አሉት። ሆኖም የተወሰኑ ጤናማ ወጣቶችንም ያጠቃል፤ ይገድላል።
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

