የኮቪድ-19 መረጃ ፦ኒው ሳውዝ ዌልስ አስፈላጊ የሚባሉ ስራዎችን የሚሰሩ ባለሙያዎችን ዝርዝር ስትጨመር በቪክቶርያ ለቫይረሱ የተጋለጡ አካባቢዎች ቁጥር መጨመሩን ቀጠለ

ይህ በአውስትራሊያ ጁላይ 18.2021 የተሻሽለ የእርስዎ የኮሮናቫይርስ መረጃ ነው ።

Sehemu ya nje ya jengo la Isola katika kitongoji cha Richmond, Melbourne, Sunday, July 18, 2021.

Mamlaka wa afya wa Victoria wamefunga jengo la Isola katika kitongoji cha Richmond, baada ya mkaaji kupatwa na Covid-19. Source: (AAP Image/James Ross)

ኒውሳውዝ ዌልስ በፌርፊልድ ፤ ካንተርበሪ - ብላክታወን አና ሊቨርፑል የሚኖሩ ነዋሪዎች በስራ ሳቢያ ከአካባቢያቸው እንዲወጡ የሚያስችላቸውን የተፈቀዱ የስራ መስክ  ዝርዝሮችን ጨመረች ።

በቪክቶሪያ በኮቪድ-19 የተጋላጡ አካባቢዎች ቁጥር መጨመሩ ቀጠለ ።

ኒውሳውዝ ዌልስ  105 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦችን ቁጥር ያስቆጠረች ሲሆን ፤ ከነዚህ ውስጥ 66 የሚሆኑት ቀድሞ ከታወቀ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ናቸው ፤ በአንጻሩ የቀሩት 33 ተያዦች ምንጭ እስከ አሁንም ደረስ ያልታወቀ እና በምርመራ ላይ የሚገኝ ነው ። በተያያዘም እድሜያቸው በ90ዎቹ ውስጥ ያሉ አንዲት ሴት የደቡብ - ምስራቅ ሲድኒ ነዋሪ ህይወታቸው አልፏል ።

በፌርፊልድ ፤ ካንተርብሪ - ብላክታወን አና ሊቨርፑል አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው መውጣት የተከለከሉ ሲሆን ፤ ነገር ግን በጤና ክብካቤ ፤ በድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የገበያ ማእከላት ፤ በመጠጥ መሸቻ ሱቆች ፤ አንስተኛ ሱቆች ፤ የጋዜጣ መሸጫዎች ፤ ቢሮዎች፤ የቤት እንሣት አገልግሎት መስጫዎች እና የአትክልት ስፍራ የሚሰሩ ባላሙያዎች መውጣት ተፈቅዶላቸዋል ።

ከሰኞ ጁላይ 19  ከጠዋቱ  12.01  ጀምሮ የግንባታ ስራዎች ፤ አስቸኳይ ያልሆኑ የጥገና ስራዎች ፤ የጽዳት አገልግሎት እና የቤት ውስጥ ጥገና ስራ የሚቋረጥ ይሆናል ። ይህ ገደብ በኒውሳውዝ ዊልስ እስከ 500,000 የሚሆኑ የግንባታ ሰራተኞችን ስራ እንደሚያስተጓጉል ከውዲሁ ተገምቷል ።

በአካባቢዎት ስርጭቱ ያላበትን ቦታ ለማወቅ ዝርዝሮቹን ወይም ካርታውን  ይመልከቱ፦  locations of the cases  በአሁን ሰአት የተቀመጠው ገደብ እስከ አርብ ጁላይ 30 እንደሚቆይ ይጠበቃል ።

ቪክቶርያ

ቪክቶርያ 16 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦችን ቁጥር ያስመዘገበች ሲሆን ከነዚህም መካከል ሁለቱ ከውጭ አገር በመጡ ሰዎች ሳቢያ የመጡ ናቸው ።  በአሁን ሰአትበቪክቶሪያ ያለው የቫይረስ ተያዦች ቁጥር 70 ደርሷል።

215 የሚሆኑ አካባቢዎች ለቫይረሱ የተጋላጡ መሆናቸው ታውቋል ። በቅርብ ከታወቁት አካባቢዎች መካከለም አልቶና ሜዶውስ ፤ ኪው ፤  እና ትሩጋኒና ይገኙበታል።

የደቡብ ምስራቅ ፊሊፕ አይላንድ አካባቢ ነዋሪዎችም ምርምራ እንዲያደርጉ ግፊት ተደርጎባቸዋል ። በአካባቢዎት ስርጭቱ ያላበትን ቦታ ለማወቅ ዝርዝሮቹን ውይም ካርታውን  ይመልከቱ ይመልከቱ፦  locations of the cases  ለአምስተኛ ጊዜ የተጣላውም ገደብ በመጪው ማክሰኞ ጁላይ 20 ከምሽቱ 11፡59 ላይ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል ።

ባለፉት 24 ሰአታት በመላው አውስትራሊያ

  • በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ እና ኩዊንስላድ በማህበረሰቡ ውስጥ ምንም የተላለፈ ቫይረስ የለም
  • በደቡ አውስስትራሊያ ወደ 100,000 የሚደርስ ክትባት አደላይድ ሾው ግራውንድ በዌይቪል ደርሷል ።
  • ታዝማንያ ድንበሯን ለሁሉም የኒውሳውዝ ዌል ነዋሪዎች ዝግ አድርጋለች
የኢድ አላድሀ በአል ( የመስእዋትነት በአል) ሰኞ ጁላይ 19 የሚጀምር ሲሆን በበአሉ የጸሎት ስነ ስራት ወቅትም ራስን እና ሊሎችን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎችን መውሰድ ይገባል ፦

  • ጸሎትን ከቤት ማድረግን ይምረጡ
  • በርካታ ሰዎች ከሚገኙበት ስፍራ ከመሄድ ይታቀቡ
  • የፊት መሸፈኛ ጭንብልን ያድርጉ
  • የርስዎን የመስገጃ ምንጣፍ ይጠቀሙ
የኮቪድ-19 አፈታርኮች

ጤነኛ ወጣቶች በኮቪድ-19 አይያዙም ፡ የሚገድለውም  አዘውንቶችን እና የጤና ቸግር ያለባቸውን ብቻ ነው ።

የኮቪድ-19 እውነታ

የእድሜ ባለጸጋዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል እንዲሁም ተያያዝ የጤና ችግር ያለባቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል ፤ ነገር ግን ጤነኛ ወጣቶችንም ይጎዳል እንዲሁም ይገድላል ።

ለይቶ ማቆያ ፤ ጉዞ፣ የመመርመሪያ ክሊኒኮች ፤ እና የወረርሽኝ ጊዜ ክፍያ

የለይቶ ማቆያ እና የመመርመሪያ ክሊኒኮች የሚመሩት እና ተግባራቸውን የሚከውኑት  በክልሎቹ እና ግዛቶቹ መንግስታት ነው ፦

ACT Transport and Quarantine
ወደሌላ አገር መጓዝ ከፈለጉም እና ፈቃድን ለማግኛት ፤ በኦንላይን ፈቃድን  ይችላሉ Click here     

ከአውስትራሊያ ውጪ እንዴት ማጓዝ እንደሚችሉ ተጨማሪ ማረጃን ማግኘት ይችላሉ ። ኣለማቀፍ በረራዎችን በተመለከተ ጊዜያዊ የሆኑ እርምጃዎች በየጊዜው በመንገስት የሚከለሱ እና የሚሻሻሉ ናቸው ስለሆነም ድረገጽን  Smart Traveller ይመለከቱ ።

ዜናዎችን እና መረጃዎችን ከ 60 በላይ ቋንቋዎች ከ sbs.com.au/coronavirus ያግኙ

በሚኖሩበት ክልል እና ግዛት ያለውን ጠቃሚ መረጃ ከ  NSW, VictoriaQueenslandWestern AustraliaSouth AustraliaNorthern TerritoryACTTasmania.  ያግኙ

የኮቪድ-19 ከትባትን በተመለከተ በቋንቋዎ መረጃን ከ  COVID-19 vaccine in your language.  ያግኙ

የኒውሳውዝዊልስ የመድብለ ባህል ጤና ክህለ ተግባቦት አገልግሎት ትርጉም መረጃዎችን  በተመለከተ ፦

የእያንዳንዱ ክልል እና ግዛት የመመርመሪያ ክሊኒኮችን በተመለከተ ፦

NSW 
ACT 
የእያንዳንዱ ክልል እና ግዛት የወረርሽኝ ጊዜ ክፍያን መረጃ በተመለከተ፦

NSW 
ACT 

Share

Published

Updated

By SBS/ALC Content
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service