የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን በሙከራ ፕሮግራም ልታስገባ ነው

*** ቪክቶሪያ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 59 ላሉ ከትባት ልትሰጥ ነው

COVID-19 update

Victorian Police officers patrol through Bourke Street Mall ahead of a planned rally in Melbourne, Friday, September 24, 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ አንድ ሶስተኛ ልጆች የመጀመሪያ ክትባታቸውን ተከትበዋል
  • ቪክቶሪያ የሞደርና ክትባት ስርጭት መጨመሩን አስታወቀች
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ የተጋላጭነት ሥፍራዎች ቁጥር እየናረ ነው
  • የክትባት መመዘኛን የሚያሟሉ ሃምሳ ፐርሰንት አውስትራሊያውያን ሙሉ ክትባት ተከትበዋል

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,043 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ፋይዘር፣ ሞደርና እና አስትራዜኔካ ሙሉ ክትባቶችን የተከተቡ 500 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን በሙከራ ፕሮግራም ልታስገባ ነው። 

የኮቪድ-19 ቫይረስ ናሙናዎች በምዕራባዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ Lightning Ridge በደቡባዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ Jindabyne በደቡባዊ ቴብላንድስ Crookwell እና በሰሜናዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ South Lismore ተገኝተዋል። 

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 733 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 84 ፐርሰንቱ ዕድሜያቸው ከ50 በታች የሆኑ ናቸው። የአንድ ሰው ሕይወም አልፏል።

የጤና ሚንስትር ማርቲን ፎሊ በመላው ቪክቶሪያ ከ700 በላይ መድኃኒት ቤቶች በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ከ 300,000 በላይ የሞደርና ክትባቶች እንደሚደርሷቸው አስታወቁ። እንዲሁም፤ ከ 32,000 በላይ ተጨማሪ ሞደርና ክትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 59 ላሉ መከተቢያነት ለተንቀሳቃሽ የክትባት ጣቢያዎች ይሰጣሉ።  

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 19 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች።

አንዲት በሰሜን ካንብራ ያለ የካልቫሪ ሄይደን የተጠዋሪ ማኅበረሰብ ነርስ በኮቪድ-19 ተይዛለች። የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የተጋላጭነት ሥፍራዎች 450 ደርሰዋል exposure locations

የኮቪድ-19  ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ to book your COVID-19 vaccination.                                                                                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የታዝማኒያ የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራ ዛሬ ጀምሯል። መንገደኞች በድንጋጌው መሠረት ከኮቪድ-19 ነፃ መሆናቸውን ማረጋጋጫ ማቅረብና ከአውሮፕላን ማረፊያ የግል እንጂ የሕዝብ ትራንስፖርት ግልጋሎትችን አለመጠቀም ይጠበቅባቸዋል። 

Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service