የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 20,794 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቁ፤ የሆስፒታል ሕሙማን ቁጥርም ንሯል

*** ቪክቶሪያ ውስጥ 8,577 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

COVID-19 update

Health care workers administer COVID-19 PCR tests at the St Vincent’s Drive-through Clinic at Bondi Beach in Sydney. Source: Getty

  • በመላው አውስትራሊያ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሆስፒታል የተዳረጉ ሕሙማን ቁጥር እየናረ ነው። ትናንት እሑድ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 1,066 ደርሶ የነበረው የሆስፒታል ሕሙማን ቁጥር ዛሬ 1,204 ደርሷል 
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የኮቪድ-19 የፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ታካሚዎች ከ83 ወደ 95 ከፍ ብሏል። ቪክቶሪያ ውስጥ 491 በኮሮናቫይረ የተጠቁ ሕሙማን ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ ሲሆን በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል የአየር መተንፈሻ ተገጥሞላቸዋል 
  • የጤና አገልግሎቶች ሠራተኛ ማኅበር የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሆስፒታል የጤና ሠራተኞች በሥራ ብዛት ሊሰላቹና የጤና ሥርዓቱም ከሁለት እስከ ሶስት ባሉ ወራት በብርቱ ፈታኝ ሁነት ላይ ሊደርስ እንደሚችል አሳሰበ
  •  በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ የፌዴራል መንግሥቱ 84 ሚሊየን ፈጣን መመርመሪያዎችን (RATs) ለግዢ እንዳዘዘና ከፍለ አገራትም ተጨማሪ አቅርቦቶችን እንደሚያገኙ ገለጡ
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ፈጣን መመርመሪያዎች በቅርብ ንኪኪ ለተፈረጁ ሰዎች በነፃ ሊሰጥ እንደሚችልና ሆኖም ለሁሉም ሰው በነፃ እንደማይሰጥ አስታወቁ 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 20,794  ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ቪክቶሪያ ውስጥ 8,577 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

 ኩዊንስላንድ 4,249 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ አንድ ሰው ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርጓል።

ታዝማኒያ 466 ሰዎች ተጠቅቶባታል።

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 514 ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

Find out what you can and can't do in your state or territory

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language

 

 

 


2 min read

Published

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now