- ለኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች ተጨማሪ ሁለት ክፍያዎች ይፋ ሆኑ
- በሜልበርን የተጣለው ገደብ ለተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ተሸጋገረ
- በኖርዘርን ቴሮቶሪ የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ገደብ ተጣለ
- በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አስራ ዘጠኝ ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ በኩዊንስላንድ ምንም ሰው አልተያዘም
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 478 ነዋሪዎቿ በማህበረሰብ ውስጥ ባለ የኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ፤ ሰባት ሰዎችም ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዎል ፡፡
መንግስት የኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ደርጃ ታይባቸዋል በማለት ለይቶ ባወጣቸው አካባቢ የሚኖሩ እና የኮቪድ -19 ምልክቶችን ላሳዩ ፤ ምርመራን ለሚያደርጉ እና ራሳቸውን ለየተው ማቆየት ለሚጠበቅባቸው A test and isolate payment እድሜያቸው ከ 17 አመት በላይ ለሆኑ ሁሉ የ $320 ክፍያን ማግኘት ይችላሉ ፡፡
የጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው እና ሌሎች የመግስት ክፍያዎችን የማያገኙም የድንገተኛ ጊዜ ክፍያን $400 በቀይ መስቀል አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ ፡፡
ተጨማሪ 530,000 የፋይዘር ክትባቶች በሲድኒ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅተዋል በተባል 12 አካባቢዎች 12 Sydney’s worst-affected local government areas የሚዳረስ ሲሆን እድሜያቸው ከ 20 እስክ 39 ለሆኑ ነዋሪዎች ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ለክትባትዎ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ቀጠሮን የያዙ ፦ vaccination appointment.
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 22 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። ከነዚህ ውስጥ አምስቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። እንዲሁም ስምንቱ አስተላልፊ በሆኑበት ወቅት በማህበረሰቡ ውስጥ የቆዩ ናቸው ፡፡
በሜልበርን የተጣለው ገደብ እስከ ሀሙስ ሴፕቴምበር 2 ከምሽቱ 11:59 ድረስ የተሸጋገረ ሲሆን ከዛሬ ከምሽቱ 3:00 የሚጀምር የሰአት እላፊ ገደብም ታውጇል ፡፡
በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination centres.
ያለፉት 24 ሰዓታትበአውስትራሊያዙሪያ
- ግሬተር ደርዊን እና ካተሪን ሪጅን በማህበረሰብ ውስጥ የታየ አንድ የኮሮናቫይረስን ተከተሎ ለ72 ሰአት የሚቆይ እና ፈጣን የሚባል ገደብ የተጣለ ሲሆን ፤ ገደቡም በአካባቢያቸው ባለው ሰአት አቆጣጠር ከእኩለቀን ጀምሮ በተግባር የሚውል ነው፡፡
- በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አስራ ዘጠኝ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሲሆን የሁለት ሳምንት ተጨማሪ ገደብም ተጥሏል ፡፡
ወሸባ፣ጉዞ፣የክሊኒክምርመራናየወረርሽኝአደጋክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permit, Overseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

