የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ 6.8 ሚሊየን ክቶባቶችን አለፈች

*** "ምንጫቸው ለጊዜው ካልታወቁት በተለይም ሆብሰንስ ቤይ፣ ዊንድሃምና ሂዩም የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች በስተቀር 'አብዛኛው የወረርሽኙ ተዛማችነት በቁጥጥር ስር ነው ያለው'" - የቪክቶሪያ ዋና የጤና መኮንን ፕ/ር ብሬት ሳተን

COVID-19 update

Premier Gladys Berejiklian and NSW Chief Health Officer Dr Kerry Chant during a COVID-19 update in Sydney, Monday, August 30, 2021. Source: AAP

  • ኮቪድ-19 በኒው ሳውዝ ዌይልስ ምዕራብ ትራንጊ ዌስት እና ባይሮን ቤይ ተከሰተ
  • ቪክቶሪያ ውስጥ በአብዛኛው በቫይረስ ተጠቅተው ያሉት ዕድሜያቸው ከ 40 በታች ያሉ ናቸው
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ለፋይዘር ክትባት መመዘኛዎችን አሰፋች
  • የከባድ ጭነት መኪና ሾፌሮች ኩዊንስላንድ ውስት ተቃውሞ አሰሙ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,290 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 883ቱ ፐርሰንት በላይ የምዕራባዊና ደቡባዊ ሲድኒ ነዋሪዎች ናቸው። አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። 

እንደራሴ በርጂክሊያን ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ጎልማሶች ውስጥ ሁለት ሶስተኞቹ የመጀመሪያ ዙር ክትባት መከተባቸውንና 36 ፐርሰንቱ የሁለተኛ ዙር ክትባቶችን መከተባቸውን ተናግረዋል። በወርሃ ኦክቶበር 70 ፐርሰንት ያህል ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ሊከተቡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቷል።

የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች የሆኑ ሠራተኞች፣ ዕድሜያቸው ከ16- 39 ሆኖ ነዋሪነታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ለሆኑና ነዋሪነታቸው ወይም የሥራ ገበታቸው ስጋት ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች ሆኖ በሕፃናት ክብካቤ፣ የግብረ አካል ጉዳተኞችና የምግብ ሠራተኞች ዘርፍ ለሆኑ የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል authorised workers who live in a LGA of concern,  people aged 16-49 who live in a LGA of concern and childcare, disability and food workers who live or work in a LGA of concern  

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 73 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 21ዱ ቫይረሱ ከተስፋፋባቸው ሥፍራዎች አይደሉም። በጠቅላላው ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረስ ተይዘው ካሉት ሰዎች ውስጥ ሶስት አራተኛዎቹ ዕድሜያቸው ከ40 በታች ያሉ ናቸው።

ዋና የጤና መኮንን ፕ/ር ብሬት ሳተን ምንጫቸው ለጊዜው ካልታወቁት በተለይም ሆብሰንስ ቤይ፣ ዊንድሃምና ሂዩም የአካባቢ መንግሥት ቀዬዎች በስተቀር 'አብዛኛው የወረርሽኙ ተዛማችነት በቁጥጥር ስር ነው ያለው' ሲሉ ገለጡ።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 12 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ስድስቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። 

ዋና ሚኒስትር አንድሩ ባር  ዕድሜያቸው ከ16-29 ያሉ "በመጪዎቹ ቀናት" ውስጥ የፋይዘር ክትባትን በመንግሥት የመከተቢያ ክሊኒኮች ውስጥ መከተብ እንደሚችሉ አስታውቁ።

የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን የሚያሟሉ መሆንዎን ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccination.

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የኩዊንስላንድ ከባድ የጭነት መኪና ሾፌሮች በጎልድ ኮስት እና ብሪስበን መካክል የሚገኘውን አውራ ጎዳና ዘግተው ገደቦች እንዲነሱና ወሰኖች እንዲከፈቱ ጠይቀዋል
  • ሁሉም ዕድሜያቸው ከ 16 እስከ 39 ያለ አውስትራሊያውያን የፋይዘር ከትባትን ለመከተብ መመዘኛዎችን እንደሚያሟሉ ተገለጠ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 


3 min read

Published

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now