የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ከሰኞ ጀምሮ ሙሉ ክትባት ለተከተቡ ነዋሪዎቿ የተወሰኑ ገደቦችን አላላች

***የቪክቶሪያ ባቡር ግልጋሎት ተገታ

COVID-19 update

Source: AAP

  • ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በቅርቡ ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸው ባይታወቅም ኮቪድ-19 ተከስቷል
  • የቪክቶሪያ  V/Line ባቡር ግልጋሎት ተገታ
  • አውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ ተጨማሪ የክትባት ቀጠሮ ስንዱ ሆኖ አለ
  • ኩዊንስላንድ አንድ ሰው በቫይረስ የተጠቃባት መሆኑን አስታወቀች

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,542 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ዘጠኝ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። 

ከሰኞ ሴፕቴምበር 13 ጀምሮ በ12ቱ የስጋት አካባቢ መንግሥት ነዋሪዎችን ስያካትት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ከአምስት ያልበለጡ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ መሰባሰብ ይችላሉ 12 local government areas (LGAs) of concern በ12ቱ የስጋት አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑና ሙሉ ክትባት የተከተቡ አብረዋቸው በአንድ ቤት ከሚኖሩ የቤተሰብ አባሎቻቸው ጋር በመሆን በቀን ለሁለት ሰዓታት ለሽርሽር ወይም ለመዝናናት እንዲሁም ላልተወሰነ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከቤታቸው መውጣት ይችላሉ። 

ኮቪድ-19 በታምዎርዝ፣ ላይትኒንግ ሪጅ፣ ግሌን ኢነስ፣ ካልቡራ ቢች እና ሞሩያ የቆሻሻ ፍሰት አካባቢዎች ተከስቶ ተገኝቷል።  

ከሰኞ ሴፕቴምበር 13 ጀምሮ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ሚኒስቴር በዕለታዊው የ11:00 am ፕሬስ ኮንፈረንስ ምትክ የኦንላይን ቪዲዮ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 334 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 149ኙ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል። 

ከሳውዘርን ክሮስ ባቡር ጣቢያ ተነስቶ ወደ ጊፕስላንድ ይጓዝ የነበረ ባቡር ሾፌር በኮሮናቫይረስ በመያዙ ሳቢያ ሃያ የ V/Line services ተገትተዋል። የግልጋሎቶቹ መገታት ምናልባትም እስከ 100 ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 24 ነዋሪዎች ተጠቅተዋል፤ ስድስቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

ባለስልጣናት ሰዎች ይቅስያዙትን ቀነ ቀጠሮ ለመለወጥ  MyDHR system  እንዲጠቅሙ አሳሰቡ። ከ30,000 በላይ ተጨማሪ ቀጠሮዎች ለተከታቢዎች ክፍት ናቸው።                                                                                                   

ለክትባትዎን ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccination 

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ብሪስበን ሰኒባንክ በሚገኘው ቅዱስ ቶማስ ሞር ኮሌጅ የታደመ አንድ ታዳጊ ወጣት በቫይረስ መያዙን አስመዘገበች።

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 

 


3 min read

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now