የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች የገደቦችን መርገብ ተከትለው ቸል እንዳይሉ ማሳሰቢያ ተሰጠ

*** ቪክቶሪያ ውስጥ 473 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቁ

COVID-19 update

Police patrol Bondi beach, in Sydney, Saturday, September 11, 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ዕድሚያቸው ከ12 በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሐኪሞች ዘንድ መከተብ ይችላሉ
  • ኮቪድ-19 ቪክቶሪያ ውስጥ በባቡር ግልጋሎቶች ላይ ብርቱ መስተጓጎልን አስከትሏል
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መከተብ እንደሚችሉ አስታወቀች
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸው ተመዘገበ 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,257 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

ቫይረስ በይበልጥ የተስፋፋባቸው ክፍለ ከተሞች Greenacre, Auburn, Yagoona, Liverpool, Punchbowl, Guildford, Redfern, Bankstown, Condell Park and Busby መሆናቸው ሲገለጥ፤ በግሌብና ረድፈርን ክፍለ ከተሞች በየዕለቱ በቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሔዱም ተነገሯል። 

ከዛሬ ጀምሮ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያለ ልጆች ጠቅላላ ሐኪሞች ዘንድ መከተብ የሚችሉ ሲሆን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮም ሞደርና ክትባትን በየመድኃኒ ቤቶች መከተብ ይቻላል።

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች በቡድን እስከ አምስት ሆነው መገናኘት ይችላሉ።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 473 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል።

ትናንት ለሊቱን አራት የሜልበርን ሕፃናት ክብካቤ ማዕከላት በከፍተኛ ተጋላጭነት ዘርፍ ተፈርጀዋል። exposure sites አምስት V/Line ባቡር ሾፌሮች በቫይረስ በመያዛቸው ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ራሳቸውን እንዲያገሉ በመደረጉ ብርቱ የባቡር ግልጋሎቶች መስተጓጎል ተከስቷል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

13 የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ነዋሪዎች በቫይረስ ተየዘዋል።  

ከሴፕቴምበር 20 ጀምሮ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 የሆነ ልጆች በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ መንግሥት ክሊኒክ ዘንድ የክትባት ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። 

የኮቪድ-19 ክትባት መመዘኛን ያሟሉ እንደሁ ለማረጋገጥ ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccination.                             

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ከአንድ የብሪስበን ትምህርት ቤት ጋር ተያይዞ በቫይረስ ከተጠቃችው ግለሰብ ጋር ንኪኪ ያላቸው ሁለት ግለሰቦች በቫይረስ ተያዙ
  • የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉ ሞደርና ክትባትን እንዲከተቡ ምክረ ሃሳቡን ሰጠ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 

 

 


3 min read

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now