የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ኩዊንስላንድ ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተጠቁባት አስታወቀች

*** በኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 239 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙባት መሆኑን አመለከተች

COVID-19 update

Queensland Chief Health Officer Dr Jeannette Young speaks to the media during a press conference in Brisbane, Sunday, August 1, 2021. Source: AAP

  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለስልጣናት ለ80 ፐርሰንት የክትባት መጠን ተለሙ
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ በዴልታ ቫይረስ የተቁ ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር 18 ደረሰ
  • ቪክቶሪያ ውስጥ አራት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሁሉም ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው
  • ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ከሆኑ አውስትራሊያውያን ውስጥ አርባ ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 239 ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባትና 61 ያህሉ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት እንደሆነ ገለጠች። ከተያዙት ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የቫይረሱ ምንጭ ገና አልተለየም።

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ተወካይ ዶ/ር ጀርሚ ማክአነልቲ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተው የፅኑዕ ህሙማን ክፍሎች ውስጥ ሕክምና እየተደረገላቸው ካሉት 54 ሰዎች ውስጥ 49ኙ ክትባት ያልተከተቡ እንደሆኑ ተናገሩ።

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን የኒው ሳውዝ ዌይልስ መንግሥት የብሔራዊ ካቢኔው ከአዋቂ አውስትራሊያውያን ውስጥ ከ70 እስከ 80 ፐርሰንት የመከተብ ትልምን መቀበሉን ገለጡ። 

የክትባት ሰጪ ክሊኒኮችን ለማግኘት ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.

ኩዊንስላንድ

ኩዊንስላንድ በዛሬው ዕለት ዘጠኝ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን አስመዝግባለች። ቁጥሩ ከአንድ ዓመት በላይ ኩዊንስላንድ ውስጥ ከተከሰተው የላቀ ነው።  

የኩዊንስላንድ ዋና የጤና ኃላፊ ዶ/ር ጃኔት ያንግ “ቁጥሮቹ በፍጥነት እያሻቀቡ ነው” ብለዋል። አክለውም፤ የማኅበረሰብ አባላት ምርመራ እንዲያካሂዱ አበረታተዋል።  

ቫይረሱ የተስፋፋባቸው የደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ አካባቢዎች ለሶስት ቀናት ገደብ ተጥሎባቸው ያሉ ሲሆን የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት ብቁ ሁኔታዎች ያሟሉ ሆነዋል። 

ቫይረስ የተስፋፋባቸውን አካባቢዎች ለማወቅ ይህን ይጫኑ list of exposure sites.

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ቪክቶሪያ ውስጥ አራት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሁሉም ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው
  • ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ከሆኑ አውስትራሊያውያን ውስጥ አርባ ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት መከተባቸውን አንድ አዲስ አሃዛዊ ሪፖርት አመለከተ

 


ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory


3 min read

Published

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now