- ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 61 ሰዎች በቫይረስ ተይዘውባታል፤ በመላው ክፍለ አገሪቱ ላይ ገደብ ተጥሏል
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽ ከተከሰተ ወዲህ ከፍተኛው በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ተመዘገበ
- ኩዊንስላንድ አንድም ሰው በቫይረስ ያልተያዘበትን ሁለተኛ ቀን አስቆጠረች
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ስምንት ሰዎች በቫይረስ የተጠቁባት ሲሆን አንዳቸውም የማኅበረሰብ ተጋቦት አይደሉም
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 825 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን በዛሬው ዕለት አስታወቀች፤ የሶስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል። ሟቾቹ አንድ 90ዎቹ ውስጥ የነበሩና ያልተከተቡ አረጋዊ፣ አንድ በ80ዎቹ የነበሩ ሙሉ ክትባት የተከተቡና አንዲት በ90ዎቹ ዕድሜ ያሉና አንድ ጊዜ ብቻ የተከተቡ አረጋዊት ይናቸው።
vaccination appointments ቫይረስ ተስፋፍቶ ባለባቸው የአካባቢ መንግሥት ሥፍራዎች ነዋሪ ሆነው ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 39 ያሉ ግለሰቦች የኮቪድ-19 ፋይዘር ቀጠሮ አስይዘው መከተብ ይችላሉ።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 61ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 39ኙ ወሸባ ገብተው ያሉ ናቸው።
ሪጂናል ቪክቶሪያ ውስጥ በርካታ ሰዎች በቫይረስ መያዝን ተከትሎ ከዛሬ 1pm ጀምሮ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ገደብ ተጥሏል።
ከሰዓት ዕላፊ በስተቀር ሜልበር ላይ ተጥለው ያሉት ገደቦች በሙሉ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ የፀኑ ይሆናሉ።
የመመርመሪያ ጣቢያዎችን ማወቅ ከፈለጉ ይህን ይጫኑ list of exposure sites በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination centres.
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ስምንት ነዋሪዎች በኮቪድ-19 መጠቃትን ተከትሎ ዕድሚያቸው ከ12 ዓመት ጀምሮ ያሉ ታዳጊ ወጣቶችን በዚህ ዓመት መጨረሻ ለመከተብ ዕቅድ ተይዟል።
- ኩዊንስላንድ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አንድም ሰው በቫይረስ ያልተያዘባት ሲሆን ከ16 ዓመት በላይ ያሉ ነዋሪዎቿ እንዲከተቡ ባለ ስልጣናት ጥሪ አቅርበዋል።
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤NSW Travel & transport and QuarantineVIC Travel permit, Overseas travellers and QuarantineACT Transport and QuarantineNT Travel and QuarantineQLD Travel and QuarantineSA Travel and QuarantineTAS Travel and QuarantineWA Travel and Quarantineወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች sbs.com.au/coronavirus በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ COVID-19 vaccine in your language.
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤NSW Victoria Queensland South Australia ACT Western Australia TasmaniaNorthern Territory
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤NSW Victoria Queensland South Australia ACT Western Australia Tasmania
Northern Territory

