የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የደቡብ-ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ገደብ ረገበ

*** ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 39 ያሉ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከሰኞ ጀምሮ የአስትራዜኔካ ኮቪድ-19 ክትባትን በመጠነ ሰፊ የክትባት ማዕከላት መስጠት ይጀመራል።

COVID-19 update

Queensland Premier Annastacia Palaszczuk provides a COVID-19 update in Brisbane, Sunday, August 8, 2021. Source: AAP

  • ኩዊንስላንድ ውስጥ ዘጠኝ ሰዎች በኮቪድ-19 ተጠቅተዋል
  • Cairns እና Yarrabah ከዛሬ 4pm ጀምሮ ገደብ ተጥሎባቸዋል   
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 262 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል
  • ቪክቶሪያ ውስጥ 11 ሰዎች ተጠቅተዋል

ኩዊንስላንድ

ኩዊንስላንድ በዛሬ ዕለት ዘጠኝ ሰዎች በቫይረስ የተጠቁባት መሆኑን አስመዝግባለች። ሰባቱ ከኢንዶርፖሊ፣ አንድ ከጎልድ ኮስት እና አንድ ከኬይንስ ናቸው።

ደቡብ-ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እንደታሰበው ዛሬ 4pm ላይ ያበቃል፤ ይሁንና የፊት ጭምብል ማጥለቅን ጨምሮ የተወሰኑ ገደቦች ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ፀንተው ይቆያሉ።

የኩዊንስላንድ እንደራሴ አንስታዥያ ፓላሼ ኬይንስ ውስጥ በቫይረስ የተጠቃ አንድ የታክሲ ሾፌር ለ10 ቀናት ይሰራ የነበረ መሆኑ አሳሳቢ መሆኑን ገልጠዋል። 

በዛም ሳቢያ የኬይንስ ሪጂናል ምክር ቤትና የያራባህ አቦርጂናል ሻየር ምክር ቤት ከዛሬ 4pm ጀምሮ ለሶስት ቀናት ገደብ ተጥሎባቸዋል።    

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዛሬው ዕለት 262 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙባት ሲሆን አንድ በ80ዎቹ የነበሩ አረጋዊት ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

72 ያህሉ በቫይረሱ የተጠቁት በማኅበረሰብ ተጋቦት ነው።

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ፐንሪዝ ከተማ አካባቢ ያሉ 12 ክፍለ ከተሞች በስጋት አካባቢነት መመዝገባቸውንና ከእሑድ 5pm ጀምሮም ተጨማሪ ገደቦች የተጣሉባቸው መሆኑን አስታውቀዋል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬ ዕለት 11 ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን ሁሉም ቫይረሱ ከተዛመተባቸው አካባቢዎች ናቸው። በቫይረሱ በተጠቁበት ወቅት አንዳቸውም ወሸባ አልነበሩም።

ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 39 ያሉ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከሰኞ ጀምሮ የአስትራዜኔካ ኮቪድ-19 ክትባትን በመጠነ ሰፊ የክትባት ማዕከላት መስጠት ይጀመራል።

አውስትራሊያ ውስጥ የመጀመሪያው የሆነው መኪና ውስጥ ሆኖ የክትባት መስጫ ማዕከል ከሰኞ ጀምሮ ሜልተን በሚገኘው የቀድሞው በኒንግስ መጋዘን ይከፈታል።  

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.


ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory


3 min read

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now