የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ክፍለ አገራት የክትባት ዒላማዎችን እየተለሙ ነው

*** እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ አስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሁሉ በእያንዳንዱ የቪክቶሪያ መንግሥት ክትባት ማዕከል እንደሚገኝና መንግሥት በሚቀጥሉት አምስት ሳምንታት ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች እንዲከተቡ የሚሻ መሆኑን ገልጡ።

COVID-19 update

Victorian Premier Daniel Andrews addresses the media during a press conference in Melbourne, Friday, August 13, 2021. Source: AAP

  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ወጣት ጎልማሶች ይበልጡን የቫይረስ ተጠቂዎች ናቸው
  • ቪክቶሪያ በአምስት ሳምንታት ውስጥ አንድ ሚሊየን ሰዎችን ለመከተብ አቅዳለች
  • በአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል
  • ከአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ወደ ኩዊንስላንድ የሚጓዙ የግድ ወሸባ መግባት አለባቸው

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 390 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ 60 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ዳቦና ዋልጌት ውስጥ አዲስ በቫይረስ ከተጠቁት 25 ሰዎች ሕፃናትን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ነባር ዜጎች ናቸው። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ዲፓርትመንት ተወካይ ዶ/ር ሜሪአን ጌል ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአብዛኛው በኮቪድ-19 የተጠቁት ዕድሜያቸው ከ 20-29 ያሉት እንደሆነ ጠቅሰው ክትባት እንዲከተቡም አሳስበዋል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 15 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። አራቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። 

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ አስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሁሉ በእያንዳንዱ የቪክቶሪያ መንግሥት ክትባት ማዕከል እንደሚገኝና መንግሥት በሚቀጥሉት አምስት ሳምንታት ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች እንዲከተቡ የሚሻ መሆኑን ገልጡ።

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination centres

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ ሰባት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተውባታል። ከቅዳሜ ኦገስት 14 ጀምሮ ከአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ወደ ኩዊንስላንድ የሚጓዙ መንገደኞች የሆቴል ወሸባ ለመግባት ግድ ይሰኛሉ። 
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ባለስልጣናት ከ 3,000 በላይ በቫይረስ ከተያዙ ሰዎች ጋር የቅርብ ንኪኪ ያላቸው ሆነው መገኘታቸውንና በጥቅሉ ስድስት ሰዎች በቫይረስ ተይዘው ያሉ መሆናቸውን አስታወቁ።   
  • የታዝማኒያ ንግዶች በወሰን መዘጋት ተጎድተዋል፤ በሌሎች ክፍለ አገራት ያሉ ከኦገስት 17 ጀምሮ ለድጎማ ማመልከት ይችላሉ። 
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory


3 min read

Published

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now