የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ ታምዎርዝ ላይ ገደብ ሲጣል፤ የሪጂናል ቪክቶሪያ ገደብ ይነሳል

*** ከማክሰኞ ኦገስት 10 ማለዳ 12:01am ጀምሮ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ ይነሳል፤ የሜልበር ነዋሪዎች ያለ በቂ ምክንያት መሔድ አይችሉም።

COVID-19 vaccination

More than half of Australia's population aged 16 and above has received at least one dose of a coronavirus vaccine Source: AAP

  • ታምዎርዝ ላይ ገደብ ተጣለ፤ ባይሮን ቤይ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ይገኛል
  • የሪጂናል ቪክቶሪያ ገደብ ዛሬ እኩለ ለሊት ላይ ሊነሳ ነው
  • በአውስትራሊያ የመጀመሪያ የሆነው የሜልበርን የመኪና ውስጥ ክትባት ማዕከል ሥራ ጀመረ
  • ታዝማኒያ ውስጥ QR ኮድ ሥራ ላይ ሊውል ነው

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 283 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል። 64 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። 

ታምዎርዝ ላይ ከዛሬ 5pm ጀምሮ ለሰባት ቀናት ገደብ ተጥሏል፤ ከኒውካስል አንድ በቫይረስ የተጠቃ ሰው ወደ ሥፍራው ተጉዞ ስለነበር በርካታ የተጋላጭነት ሥፍራዎች ተለይተዋል exposure venues 

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን አንድ ሰው በኮቪድ-19 በመጠቃቱ የተነሳ ሳቢያ በባይሮን ቤይ አካባቢ ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲካሔዱ ጥሪ አቅርበዋል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 11 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል፤ ሁሉም ቫይረሱ ተከስቶ ካለባቸው አካባቢዎች ነው። 

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ከማክሰኞ ኦገስት 10 ማለዳ 12:01am ጀምሮ ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እንደሚነሳ አስታውቀዋል፤ የሜልበር ነዋሪዎች ያለ በቂ ምክንያት መሔድ እንደሌለባቸውም አስጠንቅቀዋል።

በአውስትራሊያ የመጀመሪያ የሆነው የሜልበርን የመኪና ውስጥ ክትባት ማዕከል በዛሬው ዕለት ሜልተን ውስጥ ሥራ ጀመሯል። 

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመከተቢያ ክሊኒኮችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ list of vaccination clinics.

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ኩዊንስላንድ አራት ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ መሆኑን አስመዘገበች። በደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ላይ የተጣሉ ገደቦችን ለማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ restrictions in place for South East Queensland.
  • ኬይንስ እና ያራባህ ላይ የተጣለው ገደብ ረቡዕ ኦገስት 11 ያበቃል 
  • ታዝማኒያ ውስጥ ሁሉም የኡበርና ታክሲ ግልጋሎቶች ከዓርብ ኦገስት 13  ከምሽቱ 6 pm ጀምሮ QR ኮድ የመጠቀም ግዴታ ይኖርባቸዋል
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 


3 min read

Published

By SBS/ALC Content

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now