የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ኖቫቫክስ ክትባትና ኪኒኖች ለኮሮናቫይረስ መከላከያነት አውስትራሊያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይሁንታ ተቸረ

*** ባለፉት 24 ሰዓታት በኮቪድ-19 ሳቢያ በመላው አውስትራሊያ የ49 ሰዎች ሕይወት አለፈ

COVID-19 update

Source: AP

  • የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር ኖቫቫክስ (Novavax) ኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ይሁንታውን ቸረ፤ አውስትራሊያ 51 ሚሊየን ኖቫቫክስ ክትባቶችን አዘዘች
  • የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር በተጨማሪም ተጋላጭ ለሆኑ የኮቪድ ሕሙማን ለሚውሉ ሁለት የኪኒን ዓይንቶችም ይሁንታውን ቸሯል
  • የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ፓክስሎቪድና ሞልኑፒራቪር ኪኒኖች በመጪዎቹ ሳምንታት ወደ አውስትራሊያ እንደሚዘልቁ አስታውቀዋል
  • በኮቪድ-19 ሳቢያ በመላው አውስትራሊያ የአርባ ዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሆስፒታል ከሚገኙ 2,781 የኮቪድ ሕሙማን 212 በፅኑዕ ሕመምተኞች ክፍል ይገኛሉ
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 30,825 በቫይረስ ሲጠቁ 25 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ ለሕልፈተ ሕይወት ከተዳረጉት ዘጠኝ ሰዎች ውስጥ አንዱ ስር የሰደደ ሕመም የነበረው የ 18 ዓመት ወጣት ሲሆን 16,812 በቫይረስ ተጠቅተዋል

የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤ 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 30,825 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ25 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ቪክቶሪያ ውስጥ 20,769 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 18 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

 ኩዊንስላንድ 16,812 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ ዘጠኝ ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።

ታዝማኒያ  927 ሰዎች ተጠቅቶባታል።

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 892 ሰዎች በቫይረስ መያዛቸውን አስመዝግባለች

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ here.

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

Find out what you can and can't do in your state or territory

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለ-ባሕል ጤና አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን እዚህ ያግኙ

COVID-19 Vaccination Glossary

Appointment Reminder Tool.


የክፍለ አገራት ምርመራ ክሊኒኮች

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory


2 min read

Published

Updated

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now