የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ቪክቶሪያ ውስጥ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 ፐርሰንት ደረሰ

*** ሜልበርን ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦች ዛሬ ከምሽቱ 11:59PM ላይ ይረግባሉ

COVID-19 update

Melanie Brisbane-Schilling (left) and daughter Maddie are reunited after spending two months apart after Melanie to Melbourne from Sydney. Source: Getty

  • ሜልበርን ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦች ዛሬ ከምሽቱ 11:59PM ላይ ይረግባሉ
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለንግድ ማቋቋሚያ ተጨማሪ ድጋፍ ልታደርግ ነው
  • ኩዊንስላንድ ግዙፍ 'ልዕለ ቅዳሜ' የክትባት ዘመቻ መሰናዶዋን አስታወቀች

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ ውስጥ 2,232 በኮቪድ-19 ተጠቁ፤ 12 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

ሜልበርን ላይ ተጥሎ ያለው ስድስተኛ ዙር ገደብ ማምሻውን 11:59PM ያከትማል። 

ቪክቶሪያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለዓለም አቀፍ መንገደኞች የቤት ውስጥ ወሸባ ሙከራዋን ትጀምራለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ቪክቶሪያ የ70 ፐርሰንት ዒላማዋን መምታቷን አስመልክተው ሲናገሩ፤ 

“ረጅሙ ጉዞ ቪክቶሪያ ውስጥ ተከውኗል፤ ያ ረጅም መንገድ ዛሬ ምሽት ክፍት መሆን ይጀምራል" ብለዋል። 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

 ኒው ሳውዝ ዌይልስ 372 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። የአንድ ግለሰብ ሕይወት አለፈ። 

የክፍለ አገሩ መንግሥት ለቱሪዝምና ኩነት መስክ የ$530 ሚሊየን ዶላርስ መመደቡን ካስታወቀ በኋላ ተጨማሪ ለምጣኔ ሃብት ማገገሚያ የሚውል ድጎማ እንደሚኖርም ጠቁሟል። 

ማናቸውም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ነዋሪዎች በሆቴል ቆይታቸው ወቅት የሚጠቀሙበት የ$50 Stay and Discover ቫውቸር ይደርሳቸዋል። 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre 

ኩዊንስላንድ

ኩዊንስላንድ አንድ በዚህ ወር መጀመሪያ ሜልበርን የነበረ የኡበር ሾፌር በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች።

ዋና የጤና መኮንን ጃኔት ያንግ እንደገለጡት በ30ዎቹ ያለው ሾፌር በጣሙን የታመመ በመሆኑ በቂ መረጃን ከግለሰቡ ማግኘት አዋኪ ሆኗል። 

በሌላ በኩል፤ ኩዊንስላንድ ወሰኗን ዲሴምበር 17 ከመክፈቷ በፊት በ100 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ግዙፍ የሆነ የ'ልዕለ ቅዳሜ' ክትባት ታከናውናለች።

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 28 ሰዎች በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን በጠቅላላው 425 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ከመዲናይቱ ነዋሪዎች 80 ፐርሰንቱ ሙሉ ክትባት መከተብ ጋር ተያይዞ ዛሬ ማምሻውን ተጨማሪ ገደቦች ይነሳሉ።    

ዛሬውኑ የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • ታዝማኒያ ዛሬ የ70 ፐርሰንት ዒላማዋን መትታለች።

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 

 


3 min read

Published

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now