የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ቪክቶሪያ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሬኮርድ አስመዘገበች

*** የኒው ሳውዝ ዌይልስ ዋና የጤና መኮንን ዶ/ር ኬሪ ቻንት ነዋሪዎች በሙሉ የፊት ጭምብል ማጥለቅ፣ QR ኮድ መጠቀም፣ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅና ከሁሉም በላይ የኮቪድ-19 ምልክቶች የተሰማው ግለሰብ ምርመራ ማካሄድና ራስን ማግለልን መተግበር እንደሚያሻ አሳሰቡ።

COVID-19 update

People are seen canoeing at Albert Park Lake in Melbourne, Thursday, October 7, 2021. Source: AAP

  • ቪክቶሪያ ማሕበረሰባት ወሰን ተሻግረው እንዲገናኙ ልታደርግ ነው
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሁሉም ሰው የኮቪድ ጥንቃቄ ባህሪይን ጠብቆ እንዲቀጥል አሳሰበች
  • ከ 68 ፐርሰንት የካንብራ ነዋሪዎች ሙሉ ክትባት ተከትበዋል
  • ኩዊንስላንድና ደቡብ አውስትራሊያ ገደቦቻቸውን አረገቡ

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,838 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የአምስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።

በርካታ የአካባቢ መንግሥታት Benalla, Greater Bendigo, Buloke Shire, Loddon, Yarriambiack, Hay, Edward River, Lockhart, Murrumbidgee, Wagga Waggaን ጨምሮ ወሰን መሻገር ሊጀምሩ ነው።

ባለፉት 14 ቀን በእነዚህ አካባቢ መንግሥት ቆይተው ያሉ ነዋሪዎች ያለ ምንም ፈቃድ ቪክቶሪያን ለቅቀው መውጣት ወይም መግባት ይችላሉ።   

 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

 

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 646 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። እስካሁን ከኮቪድ ጋር በተያያዘ የ414 ሰዎች ሕይወት አልፏል። 

በምዕራብ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሃንተር ኒው ኢንግላንድ ዊ ዋ፣ ኩዪሪንዲ እና ብሪዋሪና የፍሳሽ ቁሻሻ ውስጥ ቫይረስ ተገኝቷል።

ዋና የጤና መኮንን ዶ/ር ኬሪ ቻንት ነዋሪዎች በሙሉ የፊት ጭምብል ማጥለቅ፣ QR ኮድ መጠቀም፣ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅና ከሁሉም በላይ የኮቪድ-19 ምልክቶች የተሰማው ግለሰብ ምርመራ ማካሄድና ራስን ማግለልን መተግበር እንደሚያሻ አስታውቀዋል።    

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ቴሪቶሪ ካፒታል ውስጥ 40 ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል። 

በአሁኑ ወቅት ሆስፒታል ውስጥ 16 በሽተኞች ያሉ ሲሆን ስድስቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል አምስት በመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።

የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your COVID-19 vaccination.  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • ከዛሬ ዓርብ ኦክቶበር 8 ከቀትር በኋላ 4pm አንስቶ የBrisbane, Logan, Gold Coast, Moreton Bay, Townsville (including Magnetic Island), እና Palm Island ደረጃ 3 ገደቦች ላይ ካለው የተቀረው የኩዊንስላንድ አካባቢ መንግሥታት ጋር ይገጥማሉ Stage 3 restrictions  
  • የደቡብ አውስትራሊያ ደቡብ ምሥራቅ በተቀረው ክፍለ አገር ላይ ተጥለው ካሉት ደረጃ 1 ገደቦች ስር ተጠቃለለ Level 1 restrictions 

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 

 


3 min read

Published

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now