የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የቪክቶሪያ ፖሊስ ከመቶ በላይ ፀረ ክትባት ሰልፈኞችን ዘብጥያ አወረደ

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ የወሸባ ቀናትን ልትቀንስ ነው

COVID-19 update

Victoria Police detain a protester near the Royal Botanic Gardens during an anti-mandatory vaccination protest in Melbourne, Saturday, October 2, 2021. Source: AAP

  • ቪክቶሪያ ውስጥ 1,220 ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ
  • የኒው ሳውዝ ዌይልስ ባለ ስልጣናት ነዋሪዎች የብሔራዊ ራግቢ ሊግ ውድድርን ለመመልከት ሲሉ የመሰብሰብ የጤና ደንቦችን እንዳይጥሱ አሳሰቡ
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 38 ነዋሪዎች በቫይረስ ተያዙ
  • ታዝማኒያ አንድ ነዋሪዋ በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች

ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1,220 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ የሁለት ሰዎች ሕይወትም አልፏል።    

እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ የገደቦች መጣል የጤና ሥር ዓቱን ለማስጠበቅና የጤና ባለ ሙያተኞችን ለማክበር እንደሆነ አመላክተው " ለእኛ ነፃነት ማለት ለጤና ሥርዓታችን የከፋ ጊዜ ይሆናል" ብለዋል። 

ትናንትና ፖሊስ ሜልበርን ውስጥ የፀረ ክትባት ተቃውሞ ሲያካሂዱ የነበሩ 109 ሰዎችን ዘብጥያ አውርዷል።  

በሮያል ሜልበርን ሆስፒታል የፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ነርስ ሥራ አስኪያጅ ሚሼል ስፔንስ ከወርኃ ጁላይ አንስቶ እስካሁን የፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ 90 ሰዎች አንዳቸውም ክትባት ያልተከተቡ መሆናቸው ገለጡ።  

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 667 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። 10 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ሲድኒ ላይ የኮሮናቫይረስ ገደቦች ከተጣሉ 100 ቀናት ተቆጠረ።

የጤና ሚኒስትር ብራድ ሃዛርድ የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የፍጻሜ ውድድር ግጥሚያን ክመመልክት ጋር ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲያሳስቡ "ቤታችሁ ቫይረስ ከማስተላለፍ ረገድ አንዱና ዋነኛ አደገኛ ሥፍራ ሆኖ የሚቆይ ነው" ብለዋል። 

ከኦክቶበር 11 ጀምሮ ክትባት የተከተቡ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች በቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንኪኪ በሚገጥማቸው ወቅት ለ14 ቀናት ራሳቸውን ከማግለል ይልቅ ለ 7 ቀናት ብቻ ወሸባ ይገባሉ።   

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 38 ነዋሪዎች በቫይረስ መያዛቸውን አስመዘገበች። 16ቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። 
  • ከሜልበርን ወደ ሎንሴስተን በአውሮፕላን የተጓዘ አንድ ታዳጊ ወጣት በኮቪድ-19 ተይዟል።
  • ኩዊንስላንድ ውስጥ አንድም ሰው በቫይረስ አልተያዘም። በፐንሪዝ ፓንዘርስ እና ደቡብ ሲድኒ ራቢቶስ ቡድናት መካከል የሚካሄደው የብሔራዊ ራግቢ ሊግ የፍፃሜ ግጥሚያ ዛሬ ምሽት በብሪስበን ላንግ ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል። 
  • ደቡብ አውስትራሊያ ትናንት ከቀትር በኋላ ሁለት ነዋሪዎቿ በቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች።

የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

NSW Travel & transport and Quarantine

VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine

ACT Transport and Quarantine

NT Travel and Quarantine

QLD Travel and Quarantine

SA Travel and Quarantine

TAS Travel and Quarantine

WA Travel and Quarantine

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ Click here. ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ Smart Traveller ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።



በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.


የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania

Northern Territory 


የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

NSW 

Victoria 

Queensland 

South Australia 

ACT 

Western Australia 

Tasmania
Northern Territory

 

 

 


3 min read

Published

Updated

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now