የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ ቪክቶሪያ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ከአገረሸ ወዲህ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር አስመዘገበች

*** የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከዓለም በብዛት የተከተቡ ነዋሪዎች ካሏቸው ከተሞች አንዷ ሆናለች፤ በወርኃ ኖቬምበር መጨረሻ 99 ፐርሰንት ነዋሪዎቿ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

COVID-19 update

The Royal Children's Hospital in Melbourne is dealing with a coronavirus scare in its NICU unit, which cares for vulnerable newborns. Source: AAP

  • ቪክቶሪያ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ከአገረሸ ወዲህ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር አስመዘገበች 
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የሙሉ ተከታቢ ነዋሪዎቿ ብዛት 80 ፐርሰንት ሊደርስ ነው
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተጋላጭነት ሥፍራዎች ተመዘገቡ

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 1, 571 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 13 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የሜልበርን ሮያል ሕፃናት ሆስፒታል ለሕመምተኛ ጠያቂ ወላጆች ፈጣን የኪቪድ መመርመሪያ ሥራ ላይ ሊያውል ነው።

ዛሬ ምሽት ላይ በሂዩም ሪጅን ሚችል ሻየር ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እንደሚነሳ የቪክቶሪያ ጤና ሚኒስትር አስታወቁ። 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ vaccination centre  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
 ኒው ሳውዝ ዌይልስ 444 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

እሑድ ዕለት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት እንደሚደርስ ይጠበቃል። 

እንደራሴ ዶሚኒክ ፔሮቴይ በነገው ዕለት በሚያካሂዱት የካቢኔ ስብሰባ ላይ በሚቀጥለው ሳምንት የሚረግቡትን ገደቦች አስመልክቶ የፍኖተ ካርታ ማሻሻያ ሊደረግ እንደሚችል አመላከቱ። የገደቦች ማሻሻያውን አስመልክቶም ዓርብ ዕለት መግለጫ ይሰጥበታል።  

ዕድሜያቸው ከ16 በላይ ከሆኑ ነዋሪዎች ውስጥ 75.2 ፐርሰንት ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሲሆን 90 ፐርሰንቱ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከትበዋል። 

Find a vaccination centre near you.

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 51 ሰዎች በቫይረስ ተጠተዋል። ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ካሉት 16 ሕሙማን ውስጥ ስምንቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች የሚገኙ ሲሆን አምስቱ በመተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።   

በአሁኑ ወቅት 370 የተጋላጭነት ሥፍራዎች ያሉ ሲሆን የካንብራ ነዋሪዎች አዲሶቹን የተጋላጭነት ሥፍራዎች እንዲለዩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል ACT COVID-19 website

ዛሬውኑ የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ book your vaccine appointment 

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • ቪክቶሪያ እየበረከተ የመጣውን የቫይረስ ሕሙማን ቁጥር ለመቋቋም ከባሕር ማዶ 1000 የጤና ክብካቤ ሠራተኞችን ልታስመጣ ነው።
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ከዓለም በብዛት የተከተቡ ነዋሪዎች ካሏቸው ከተሞች አንዷ ሆናለች፤ በወርኃ ኖቬምበር መጨረሻ 99 ፐርሰንት ነዋሪዎቿ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።  
 

 


Share

Published

By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service