የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤የዓለም ጤና ድርጅት ኦሚክሮን ቫይረስን በተመለከተ ከልክ ያለፉ ገደቦች እንዳይጣሉ አሳሰበ

*** የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከዳር እስከ ዳር የሚጣሉ ድፍን እገዳዎች የኦሚክሮንን መስፋፋት ከመግታት ይልቅ ከቶውንም በሰዎች 'ሕይወት ላይ ጫናን እንደሚያሳድር' አሳሰቡ። ቫይረሱ በአሁኑ ወቅት 23 አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል።

WHO director-general Tedros Ghebreyesus says its too early to relax

WHO director-general Tedros Ghebreyesus says its too early to relax Source: AAP

  • የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከዳር እስከ ዳር የሚጣሉ ድፍን እገዳዎች የኦሚክሮንን መስፋፋት ከመግታት ይልቅ ከቶውንም በሰዎች 'ሕይወት ላይ ጫናን እንደሚያሳድር' አሳሰቡ። ቫይረሱ በአሁኑ ወቅት 23 አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል። 
  • ድርጅቱ ለተላላፊ በሽታ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች ጉዟቸውን ቢገቱ የተሻለ እንደሚሆን አመላካች መምሪያ አውጥቷል። 
  • ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ሰባተኛ ሰው በኦሚክሮን መጠቃቱ ተገለጠ። ግለሰቡ ደቡብ አፍሪካ እንዳልነበረም ተነግሯል። 
  • የቪክቶሪያ ጤና ሚኒስትር ኦሚክሮን ማኅበረሰቡ ውስጥ ሳይዘልቅ እንዳልቀረ ጠቆሙ። እስካሁን ድረስ ቪክቶሪያ ውስጥ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልተመዘገበም። 
  • የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁትር ከፍተኛ በመሆኑ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እምብዛም እንደማያሳስብ ተናገሩ። 
  • የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አንስታዥያ ፓለሼይ ትናንት ጎልድ ኮስት ውስጥ በኮሮናቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ በጥቁር ዓርብ ዕለት በርካታ ቦታዎች መዘዋወሩን ገለጡ። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,419 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 10 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 271 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ስምንት፣ ኖርዘርን ቴሪቶሪ አንድ ሰው በቫይረስ የተጠቃባቸው መሆኑን መዝገበዋል።  

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

Find out what you can and can't do in your state or territory

ጉዞ

Information for international travellers የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  Getting help during Covid-19 from Services Australia in language


 

 

 

 


2 min read

Published

Updated

By SBS/ALC Content

Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now