ቪክቶርያ ዝቅተኛ የተባለውን የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር አስመዘገበች
በቪክቶርያ ባለፉት 24 ሰአታተ 11 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ ሁለት ሰዎችም ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተዘግቧል ።
ይህ ቁጥር ባላፉት ሶስት ወራት ከተመዘገቡት ሁሉ ዝቅተኛው እንደሆነም ተነግሯል ።
በአሁን ሰአት በቪክቶርያ 657 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋጠ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 23 ያህሉ የሚኖሩት በገጠራማ የከተማዋ ክፍሎች ነው።
የቪክቶሪያው ፕሬምየር ዳናኤል አንድሪውስ በተከታታየ የተመዘገቡትን አንስተኛ ቁጥሮች መሰረት በማድረግ ቪክቶሪያ ተስፋ እንዳላት ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ተውስደው የነበሩት እርምጃዎች እና መሰእዋትነቶች ሁሉ ፍሬ ማሳሳየታቸን ገልጸዋል ፡፡
ምክትል የጤና አፊሰር ዶ/ር ኒክ ኮትስዎርዝ እንዳሉት የተጣሉትን ገደቦች ሙሉ ለሙሉ ለማላላት ገና ረጅም ጉዞ የሚቀር እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያሻም አሳስበዋል ።
Share

