ቶኪ-በኣ ከጥንት ጀምሮ በብሔረሰቡ ዘንድ የክረምት ወራት ማብቂያና የፀደይ ወራት መቀበያ፣ የክረምቱ ጥቁር ሰማይ ወገግ ብሎ መስኩ ቡቃያ ለብሶ፣ በሰላም ላከረመው አምላክ ምስጋና የሚቀርብበት ነው ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ለSBS በላከው መግለጫ አስታውቋል።
በዓሉ መጪው ጊዜ ከቤተሰብ እስከ ሀገር የሰላም ፣ የጤና፣ የጥጋብ እንዲሆን በመመኘት፣ ችቦ በመለኮስ፣ ከየአይነቱ ምግብ ተዘጋጅቶ በታላቅ ደስታ የሚከበር የብሄሩ የቆየ ባህል ነው መረጃው እንደጠቆመው።
በበዓሉ እለት ከጥራጥሬ፣ ስራስር፣ እንስሳት ተዋጽኦ በተለይ በብሔረሰቡ ምግብ አዘገጃጀት እንደ ቅመም በሁሉም ምግብ የማይጠፋው ቆጮና ቅቤ ታክሎበት ጠግቦ ማደር የግድ ነው። ይህም የደስታ ፣ የተድላና የጥጋብ ዘመን መግባቱን ለማመልከት ነው ተብሏል።

Source: Edgetu Bezabih
የውሃ መቅጃ እንስራ፣ የምግብ ማቆያዎች ጨምሮ ቤት ያሉት ሁሉም ዕቃዎች በሚይዟቸው አይነት ሙሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል ፡ የሙላት ዘመንነቱን እንዲያበስሩ።
እሳቤውም አድሱ አመት ሙሉነት፣ ጥጋብ፣ ደስታና አዲስ ተስፋ እንድሆን የሚል ነው። ይህ የጥጋብ በዓል ነው፣ የባህል እሴታችን ነው።
የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤቱ እንዳለው ዛሬ የምናከብረው ብቻ ሳይሆን ተመራማሪዎችና ፀሐፊዎችን ጨምሮ፣ ለትውልድ ማሸጋገር ያለብን ሀብታችን ነው ፡ የበኩላችንን እንወጣ ብሏል።
የዘንድሮን በዓል እንደወትሮ በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት በአዳራሽ በፓናል ውይይት እና በሌሎችም ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ መከበሩን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
Share

