SKIP TO MAIN CONTENT

በአምስት አውሮፕላኖች በመታገዝ የአንበጣ መንጋን የመከላከሉ ስራ እየተከናወነ ነው

*** የአንበጣው መንጋ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌ፣ በትግራይ፣ አፋር ክልሎችና በድሬዳዋ መስተዳድር ተከስቷል

Desert locusts
Source: PD

1 min read

Published

By Stringer


Skip to article content

በአምስት የኬሚካል መርጫ አውሮፕላኖች፣ በ127 የኬሚካል መርጫ መኪኖች፣ በ3 ድሮኖች እንዲሁም በሰው ኃይል በመታገዝ የአንበጣ መንጋን የመከላከሉ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በቅርቡ ከገቡት አራት አውሮፕላኖች መካከል ሶስቱ ኬሚካል የመርጨት ስራ እየሰሩ መሆኑንና አንዱ አውሮፕላን ግን የታንከር ገጠማ እየተከናወነለት መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

የአንበጣው መንጋ የታየበት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌ፣ በትግራይ፣ አፋር ክልሎች እና በድሬዳዋ መስተዳድር ላይ መሆኑን ዶ/ር ማንደፍሮ ተናግረዋል።

ከአምስቱ አውሮፕላኖች መካከል ሁለቱ የቅኝት መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ መጠን ያለው የአንበጣ መንጋ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተ ቢሆንም፣ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ለመቆጣጠር እንደተቻለም ሚኒስቴር ዴኤታው ገልጸዋል።

በአፋር ክልል የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በአመዛኙ መቆጣጠር መቻሉን ዶ/ር ማንደፍሮ ተናግረዋል፡፡

የአንበጣ መንጋውን ለመቆጣጠርም በአየር፣ በድሮን፣ በመኪና እና በሰው ኃይል ርጭት እያደረግን ነው ብለዋል።

ለሙከራ ርጭት የተሰማሩ ሶስት ድሮኖች ውጤታማ የኬሚካል ርጭት እያከናወኑ መሆኑም ተገልጿል።

ኢቲቪ እንደዘገበው በዚህ አደጋ ተጎጂ የሆኑት አርሶ አደሮች ቶሎ የሚደርሱ የሰብል ዝርያ እና ማዳበሪያ ተሰጥቷቸው እንዲያመርቱ ይደረጋልም ብለዋል-ዶ/ር ማንደፍሮ።

የመከላከል ስራው በሰፊው ከተሰራ በኋላ የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now