SKIP TO MAIN CONTENT

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አውስትራሊያውያን ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ እንዲወጡ አሳሰበ

*** የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አውስትራሊያውያን የፀጥታ ሁኔታው በፍጥነት እያሽቆለቆለ ባለበት ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ በረራዎች ይኖራሉ ብለው እንዳይጠብቁም ምክረ ሃሳቡን ቸሯል።

SBS Amharic
Source: SBS Amharic

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎች በአስቸኳይ ኢትዮጵያን ለቅቀው እንዲወጡ አስቸኳይ ማሳሰቢያ አወጣ። 

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ  ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አውስትራሊያውያን የፀጥታ ሁኔታው በፍጥነት እያሽቆለቆለ ባለበት ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ በረራዎች ይኖራሉ ብለው እንዳይጠብቁም ምክረ ሃሳቡን ቸሯል። 

ከኢትዮጵያ ለመውጣት አሁን የንግድ በረራዎች እንዳሉና የከፉ ሁኔታዎች ከተከሰቱ ግና የንግድ በረራዎች ሊታገዱ እንደሚችሉ አመላክቷል።  

አዲስ አበባ የሚገነው የአውስትራሊያ ኤምባሲ ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተለ ስለመሆኑና ፖሊስ አውስራሊያውያንን ጨምሮ ለእሥራት ያበቃቸው ሰዎች መኖራቸውን እንደሚያውቅም ገልጧል።   

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያለው የጉዞ ማሳቢያ "አይጓዙ" (ደረጃ 4) ነው።   

ከኢትዮጵያ ለቅቆ መውጣትን አክሎ አስቸኳይ የቆንስላ እርዳታ የሚሹ አውስትራሊያውያን ወደ ቆንስላው የአስቸኳይ ጊዜ ማዕከል በስልክ ቁጥር +61 2 6261 3305 መደወል ይችላሉ።

ለተጨማሪ የጉዞ ማሳሰቢያ መረጃ ይህን ይጫኑ here

 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now