SKIP TO MAIN CONTENT

"በንፁኃን ዜጎች ላይ የሚካሄደው ጭፍጨፋ ፍፁም አረመኔያዊና በፍጥነት መቆም ያለበት እኩይ ድርጊት ነው" - ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

*** ከሁሉም አቅጣጫ የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመመከት የመንግስትና ህዝብ ቅንጅታዊ ርብርብ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

Deputy Prime Minister Demeke Kebede
Deputy Prime Minister Demeke Kebede Source: PD

1 min read

Published


Skip to article content

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በንፁኃን ዜጎች ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የተሰማኝን ሃዘን እየገለፅኩ፤ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ፡፡

በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ቀደም ሲል  ብሄርን፣ ሃይማኖትን እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የማድረስ ዓላማ ያላቸው ጥቃቶችና ጭፍጨፋዎች ተካሂደዋል፡፡

በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ ዞን በንፁኃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል፡፡

በተለይ የአማራን ማህበረሰብ ትኩረት ያደረገና በንፁኃን ዜጎች ላይ የሚካሄደው ጭፍጨፋ ፍፁም አረመኔያዊና በፍጥነት መቆም ያለበት እኩይ ድርጊት ነው፡፡

ድርጊቱ አስቀድሞ መዋቅራዊ በሆነ መልኩ ሲዘራ የቆየ በመሆኑ፤ ችግሩን የሚመጥን መፍትሄ በዘላቂነት ለማበጀት አስፈላጊው ሁሉ ይደረጋል፡፡

ከዚህ አኳያ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ከሁሉም አቅጣጫ የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመመከት የመንግስትና ህዝብ ቅንጅታዊ ርብርብ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now