የመቀሌ የመጨረሻው ዘመቻ ምዕራፍ መጀመሩ ተነገረ

*** "የመከላከያ ሠራዊታችን የመጨረሻውንና ሶስተኛውን የዘመቻውን ምዕራፍ እንዲፈጽም ትዕዛዝ ተሰጥቷል" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

PM Abiy Ahmed

PM Abiy Ahmed Source: Getty Images

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "የመጨረሻው የዘመቻ ምዕራፍ ተጀምሯል" በሚል ርዕስ ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 17 - 2013 ይፋ ባደረጉት መግለጫ አስታወቁ። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕወሓት ጦር ተሰባስቦ መሽጎ ያለባት መቀሌ ላይ የመከላከያ ሠራዊታቸው "ሕግ የማስከበር ዘመቻው የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ" መድረሱን የገለጡት የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት እንዲሰጡ የሰጡት የ72 ሰዓት ገደብ ያከተመ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

 

ይሁንና አያይዘውም "በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት ሰጥተዋል" ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

 

መግለጫው መንግሥት የ72 ሰዓት ገደብ ሲሰጥ ሁለት አላማዎች እንደነበሩት ሲያመለክት "በአንድ በኩል ዋና ፍላጎቱ ሕግ ማስከበር እንጅ ጦርነት አለመሆኑን መግለጥ ነው። ሁለተኛው ደግሞ የሕወሓት የጥፋት አላማ ዘግይቶም ቢሆን የገባው አንድም ሰው ከተገኘ ያንን ሰው ለማትረፍ እንዲቻል ነው" ሲል አስረድቷል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የመከላከያ ሠራዊታችን የመጨረሻውንና ሶስተኛውን የዘመቻ ምዕራፍ እንዲፈፅም ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። በዚህ ዘመቻ ለንፁሃን ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በሕዝባችን ላብ የተሰራችው የመቐለ ከተማ የከፋ ጉዳት እንዳያገኛት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል። የመቐለና የአካባቢው ህዝባችን ትጥቁን ፈትቶ በቤቱ በመቀመጥና ከወታደራዊ ዒላማዎች በመራቅ፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን" ሲሉም አሳስበዋል።

 

ቀደም ሲል የሕወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ "እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ጠብመንጃ የያዘም ያልያዘም የሚመክተው ጦርነት ነው" ብለዋል። 

 

ግማሽ ሚሊየን ያህል ሕዝብ ባላት መቀሌ ውስጥ የሚካሄደው የሁለት ወገኖች ፍልሚያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳትና ሕልፈተ ሕይወት እንዳያስከትል የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴርዝን "በትግራይ ያለው ሁኔታ በጣሙን አስግቶኛል። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግ በሁሉም ወገኖች ዘንድ የግድ መከበር አለበት። የኢትዮጵያ መሪዎች የሰላማዊ መሪዎች ደኅነንት እንዲጠበቅ፣ የሰብዓዊ መብቶችና ሰብዓዊ እገዛ ተደራሽነት እንዲከበር የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ አሳስባለሁ" አሰኝቷል።

 

ጃኑዋሪ 20 - 2020 46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት የሚሆኑት የጆ ባይደን ዕጩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም በበኩላቸው ሕወሓትና የኢትዮጵያ ባለ ሥልጣናት ግጭቱ እንዲቆም፣ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖርና ሰላማዊ ሰዎች የደኅንነት ጥበቃ እንዲያገኙ ለማስቻል አስቸኳይ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስበዋል።

Anthony Blinken
Anthony Blinken, Secretary of State nominee for Biden administration. Source: Anthony Blinken

  


2 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now