የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስቸኳይ መግለጫ

*** "በትግራይ ክልልና አዋሳኝ ቦታዎች ያለው እንቅስቃሴ የሰላማዊ ሕዝብን የሕይወትና አካላዊ ደህንነት ብሎም የሲቪል ንብረቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥል እንዲሆንና ሁሉም ወገኖች ግጭት አባባሽ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጥሪውን ያቀርባል" - ኢሰመጉ

EHRC

Dr Daniel Bekele, Chief Commissioner of Ethiopian Human Rights Commission Source: EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ - ኢሰመጉ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ ቦታዎች ያለው እንቅስቃሴ የሰላማዊ ሕዝብን የሕይወትና አካላዊ ደህንነት ብሎም የሲቪል ንብረቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥል እንዲሆን እና ሁሉም ወገኖች ግጭት አባባሽ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና መላው ኢትዮጵያውያን ግጭቱ ተባብሶ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ በሁሉም ወገኖች ላይ ግፊት እና ጫና እንዲያደርጉ ኢሰመጉ ይጠይቃል፡፡

መንግሥትም በየጊዜው በሚፈጠሩ ነገሮች ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ኢሰመጉ ይጠይቃል፡፡

ሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና ብዙኃን መገናኛ ድርጅቶች ሕዝብን ለግጭት የሚያነሳሱ እና ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የሚዳርጉ የሐሰት ዜናዎችን፣ የተሳሳቱ፣ የተዛቡ እና የተበከሉ መረጃዎችን ከመናገር እና ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ኢሰመጉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጥቅምት 25፣ 2013 ዓ.ም

አዲስ አበባ፣

ኢትዮጵያ 


1 min read

Published

Updated


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now