ምነውእንደዚህከሰብአዊነትተራወጣን? እስከመቼስይህዓይነቱኢ-ሰብአዊድርጊትይፈጸማል? ኢትዮጵያስእስከመቼየደምመሬትሆናትቀጥላለች? እኛስእስከመቼየሀዘንመግለጫእያወጣንእንዘልቃለን? በ
ምእራብወለጋየተከሰተውየሰሞኑየዘርማጥፋትወንጀልሕይወታቸውንለነጠቃቸውኢትዮጵያውያንየአማራተወላጆችየተሰማንንጥልቅሀዘንእየገለጽንበአገራቸውላይበተለያዩአካባቢዎችግፍእየደረሰባቸውካሉየአማራተወላጆችጎንሁሉምየኢሕአፓአባላትእንደምንቆምበአንክሮእንገልጻለን፡፡ፓርቲያችን፣የኢትዮጵያሕዝባዊአብዮታዊፓርቲ (ኢሕአፓ) ሰሞኑንበአማራወገኖቻችንላይየደረሰውአስከፊጭፍጨፋእጅግያሳዘነውናያስቆጣውመሆኑንበመራርሁኔታይገልጻል። ኢሕአፓበጭፍጨፋውሕይወታቸውንላጡወገኖቻችንየተሰማውንጥልቅሃዘንእየገለጸ፤ለወዳጅዘመዶቻቸውምመጽናናቱንይመኛል።
የሟቾችቁጥርየጥቃቱንግዝፈትያመላክትእንደሆነእንጂየወንጀሉመፈጸምናያለመፈጸምሊጠቀስየሚገባውጉዳይአይደለም፡፡መንግሥትግፍለሚፈጸምበትአንድዜጋውምቢሆንተቆርቋሪነትንማሳየትግዴታውነው፡፡እየሆነያለውግን፣እጅግየተለየነው፤ያለፈውንሁሉትተንበወራትውስጥየተከሰተውንሰቆቃማሰብብቻውንኢትዮጵያዊነታችንንእንድንጠራጠርአድርጎናል፡፡
ከሰብአዊነትውጭየሆነውክስተትአብሮየመኖርንናየመዋለድንታሪክየፋቀመሆኑንማየትይቻላል፡፡ለመሆኑይህሁሉሲሆንመንግሥትምንእያደረገነው? በቃልከመናገርየዘለለየሕግየበላይነትንየማስጠበቅግዴታውንሲፈጽየማይታይመንግሥትስምንስምይሰጠዋል?
ይህንንመሠልግፍናእልቂትአንድቦታላይ “በቃ!” ማለትይገባል፡፡ “ሳይርቅበቅርቡመመለስ፣ሳይደርቅበእርጥቡማቃናት” ሲገባ፣ “በእንቁላሉጊዜበቀጣሽን” እንደተባለውተመጣጣኝርምጃወስዶወንጀልንበጅምሩማስቆምሲገባ፤በቸልተኝነትማለፍአሁንለደርስንበትቅጥ-ያጣሁኔታእንዳደረሰንመቀበልግድይሆናል፡፡
በወለጋይህጥቃትየተፈጸመውዛሬአይደለም፣በባሌናበአርሲ፣በቤኒሻንጉልናበጉራፈርዳእንዲሁምበሌሎችአካባቢዎችዜጎችበዘራቸውየተነሳሲጨፈጨፉዓመታትንእያስቆጠረነው፡፡እነዚያሁሉጥቃቶችግንይኸነውየሚባልምላሽአልተሰጣቸውም፡፡ የሕግየበላይነትምበአግባቡናበትክክለኛውመጠንናልክሲከበርምአላዬንም፡፡
ተፎካካሪፓርቲዎች፣የሰብአዊመብትተሟጋቾችናሕዝቡተቃውሞአቸውንበተደጋጋሚቢያቀርቡም፣በርካታመግለጫዎችንቢሰጡም፣መንግሥትጆሮመስጠቱንያመላከቱተግባራትንሲፈጽምአልታየም፡፡ይህጆሮ-ዳባልበስአካሄድምየፖለቲካፓርቲዎችተፎካካሪነታቸውየቃላትመሆኑንናሃሳባቸውየሚደመጥለመሆኑንእንዲገነዘቡናሕዝብምበለውጡላይያለውአመኔታእየቀነሰናእየተሟጠጠእንዲሄድከማድረጉበስተቀርያስከተለውፋይዳየለም፡፡
ችግሩበቀጣይነትእየከፋየሄደባቸውየኦሮሞናየአማራየፖለቲካድርጅቶችአስርወርሙሉሲሰበሰቡቢቆዩምያመጡትውጤትየለም፡፡ይልቁንምበእነዚህአስርወራትውስጥ፣ሕዝቡበዘሩምክንያትእየተገደለናእየተፈናቀለ፣ብሎምእየተሰደደነው፡፡በመንግሥትበኩል፣በሽፍንፍንለማለፍየሚቻልችግርያለመኖሩንመረዳትየተቻለአይመስልም፤ፍርጥርጥያለውእውነትእንዲወጣም “አካፋንአካፋ፣ዶማንምዶማ” ማለትአልተቻለም፡፡
አንዳንድየመንግሥትአካላትችግርንከማቃለልይልቅየችግሩአካላት፣የፍጅቱአራጋቢዎችሲሆኑመስተዋላቸውየአደባባይሚስጥርነው፡፡ታዲያይህበሆነበትእውነታመንግሥትበቆራጥነትየሕዝቡንደህንነትይጠብቃልብሎለማመንእንዴትይቻላል? ለመሆኑለኢትዮጵያዲሞክራሲንሊያመጣተስፋየተጣለበትለውጥስ “ያሳምራልያሉትኩልዓይንአጠፋ” እንዲሉለምንሆነ?
ኢሕአፓበተደጋጋሚባወጣቸውመግለጫዎችየዜጎችንመጨፍጨፍናመሰደድተቃውሟል፡፡መንግሥትትክክለኛሚናውንእየተጫወተሳይሆንበአንዳንድሁኔታዎችበሚነደውእሳትላይቤንዚንየመጨመርክስተቶችንሊያቆምእንደሚገባናየሕግየበላይነትንማስከበርእንደሚገባውአሳስቧል፡፡ሆኖምሁኔታዎችእየተሻሻሉሳይሆንእየከፉመሄዳቸውይስተዋላል፡፡
የዜጎችንሰቆቃእያዳመጡትርጉምአልባጩኸትመጮህይሰለቻል፡፡የሃይማኖትተቋማትውግዘትናሱባኤየሕዝብጸሎትናምህላምእነሆየኢትዮጵያንስቃይለፈውሱእንዳልቻሉተመልክተናል፡፡እናምእሹሩሩሊበቃይገባል! ጥፋተኞችተገቢውንቅጣትሊያገኙ፤ሕዝቡምእፎይሊልያስፈልገዋል፡፡
በትናንትናውዕለትየተፈፀመውፍጅትበዓይነቱለየትያለመሆኑታውቋል፤ሕዝብንከቤቱለስብሰባአስወጥቶበቦንብናበጥይትማጋየቱ፤ቤትናንብረትማቃጠሉ... በርካቶችመግለጫእንዲያወጡአድርጓል፡፡ሆኖምይህቋትአይሞላም፤ከዚህቀደምየተከሰቱእልቂቶችናየሰብአዊመብትጥሰቶችከንግግርያለፈትሩፋትአላመጡም፡፡ይልቁንስሁኔታውንከስሩመመርመርናበዓይነቱለየትያለውዘር-ተኮርጭፍጨፋ (የዘር-ማጥፋት) እንዲከሰትያደረገውሁኔታምንእንደነበረእውነተኛውንምክንያትማውጣትያስፈልጋል፡፡
ሕዝብ “ትታችሁንአትሂዱ! ሊጨርሱንነው!...” ወዘተእያለሲማጸን “ታዝዣለሁ...አልቆይም!” በማለትአካባቢውንየለቀቀውየሀገርመከለካከያሠራዊትሃላፊነቱንመወጣትለምንአቃተው? ተዕዛዙንያስተላለፈውስማነው? የመከላከያሠራዊቱንእግርተከትሎየታጣቂውሃይልህዝብንስብሰባጠርቶየመፍጀትግጥምጥሞሹስእንዴትሊፈጠርቻለ? የቦንብናየመሳሪያእሩምታሲወርድናየሕዝብሰቆቃአየሩንሲሞላውየኦሮሚያክልልልዩሃይልለምንአልሰማም? የትስሄዶነበር? .... ለሚሉትጥያቄዎችትክክለኛውንመልስበመፈለግእውነተኛፍርድመስጠትእናየሕግየበላይነትንለዘሌቄታውለማስከበርይቻልዘንድየማያወላዳውሳኔመስጠትያስፈልጋል፡፡
ኢሕአፓይህየግፍተግባርበአስቸኳይመቆምይኖርበታልየሚልጽኑአቋምአለው፡፡ወንጀለኞችምታድነውለፍርድእንዲቀርቡጥሪውንያስተላልፋል።ሀገራችንኢትዮጵያምአሁንከምትገኝበትአስከፊየጸጥታሁኔታወደተሻለናወደተረጋጋሁኔታእንድትመጣናሰላምእንዲሰፍንኢሕአፓየሚከተሉትንሰባትነጥቦችወይምየመፍትሔሃሳቦችያቀርባል።
- ኢሕአፓበሥልጣንላይያለውመንግሥትከምንጊዜውምየጠነከረናየሕዝብወገናዊነቱንየሚያስመሰክርአስቸኳይእርምጃእንዲወስድያሳስባል፡፡መንግሥትያለምንምማወላወልየሕግየበላይነትንእንዲያረጋግጥናበወንጀለኞችላይያለማመንታትእርምጃእንዲወስድበአንክሮያሳስባል፡፡
- ጽንፍበረገጠየዘረኝነትአመለካከትእናጥላቻየተነሳለተሰዉኢትዮጵያንመንግሥትየሀዘንቀንእንዲሰይምምኢሕአፓይጠይቃል፡፡በሀገራችንውስጥሰላምእንዳይሰፍን፣ኢትዮጵያንደካማሀገርእንድትሆንያላሰለሰሚናበሚጫወተውሕወሃትመራሹኃይልላይምየማያዳግምእርምጃእንዲወሰድእንጠይቃለን፡፡
- በመንግሥትመዋቅርውስጥየተሰገሰጉናየአንድንብሔርየበላይነትመልሰውለማስፈንየሚጥሩአክራሪ “የተረኝነትስሜት” ከተጠናወታቸውብሔርተኞችራሱንእንዲያጸዳእያሳሰብን፤ከዚህቀደምእንደሚደረገውበሕግማስከበርሥርዓትናሂደትበማሳበብአጥፊዎችምንምሳይደርስባቸውለዓመታትናለወራትየዘለቀየፍትሕመጓተትበፍጹምሊኖርእንደማይገባኢሕአፓለመግለጽይገደዳል፡፡
- የኢትዮጵያሁኔታእንዲህከድጡወደማጡእያሽቆለቆለእናወደየትኛውምየኢትዮጵያክፍልመንቀሳቀስአስጊበሆነበትወቅት፣የሰላምእጦትአንገብጋቢበሆነበትነባራዊሁኔታላይ፣አገራዊምርጫየሚደረግበትንምህዳርማሰብእጅግከባድበመሆኑሊታሰብበትእንደሚገባበአንክሮይገልፃል፡፡
- በሀገራችንውስጥለተከሰቱትበርካታችግሮችምንጩናመሠረቱበሥራላይያለውሕገ-መንግሥትበመሆኑበአጭርጊዜውስጥ፣ሕዝቡንያሳተፈየሕገ-መንግሥትጉባዔበመጥራትመሠረታዊማሻሻያእንዲደረግበድጋሚጥሪያችንንእናስተላልፋለን፡፡
- የሀገራችንንምስቅልቅልችግሮችፈርለማስያዝናዘላቂሰላምንእውንለማድረግባለድርሻዎችንየሚያሳትፍሃገራዊውይይትበአስቸኳይእንዲጠራናየብሄራዊመግባባትሂደትምእውንእንዲሆንአበክረንእንጠይቃለን።
- መንግሥትአስቸኳይእርምጃየማይወስድእናጉዳዩንበማለባበስለማለፍየሚሞክርከሆነለኢትዮጵያሕዝብቆመናልየሚሉተፎካካሪየፖለቲካፓርቲዎችለሀገራችንየመንግሥትንያህልሃላፊነትያለብንመሆኑንበመገንዘብግዴታችንንለመወጣትመምከርናየጋራጠንካራሕብረ-ኃይልማቋቋምእንዳለብንኢሕአፓያሳስባል፡፡
በመጨረሻም፣በዚህአጋጣሚ፣በተደጋጋሚየአብረንእንሥራመልዕክታችንንኢትዮጵያእንደአገርመኖርናመቀጠልእንዳለባትከሚያምኑአገርወዳድኃይሎችጋርበመሆን፣አክራሪብሔርተኞችንመታገልየሚችልጠንካራኃይል (የጋራንቅናቄወይንምመድረክ) መመሥረትአስፈላጊነቱንናወቅታዊነቱንበማመንጥረቱንምበመጀመርሀገርናሕዝብንበጋራእንድንታደግኢሕአፓጥሪውንያቀርባል።
ኢትዮጵያአንድነቷተከብሮለዘላለምትኑር!
ኢሕአፓለተሻለነገ!
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም…. አዲስአበባ!
(በምዕራብወለጋበአማሮችላይየተካሄደውንጭፍጨፋበጥብቅእናወግዛለን!)
ጥቅምት፳፫ቀን፪ሺህ፲፫ዓ. ም
ምነው እንደዚህ ከሰብአዊነት ተራ ወጣን? እስከመቼስ ይህ ዓይነቱ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ይፈጸማል? ኢትዮጵያስ እስከመቼ የደም መሬት ሆና ትቀጥላለች? እኛስ እስከመቼ የሀዘን መግለጫ እያወጣን እንዘልቃለን? በምእራብ ወለጋ የተከሰተው የሰሞኑ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሕይወታቸውን ለነጠቃቸው ኢትዮጵያውያን የአማራ ተወላጆች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን በአገራቸው ላይ በተለያዩ አካባቢዎች ግፍ እየደረሰባቸው ካሉ የአማራ ተወላጆች ጎን ሁሉም የኢሕአፓ አባላት እንደምንቆም በአንክሮ እንገልጻለን፡፡ ፓርቲያችን፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሰሞኑን በአማራ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አስከፊ ጭፍጨፋ እጅግ ያሳዘነውና ያስቆጣው መሆኑን በመራር ሁኔታ ይገልጻል። ኢሕአፓ በጭፍጨፋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናቱን ይመኛል።
የሟቾች ቁጥር የጥቃቱን ግዝፈት ያመላክት እንደሆነ እንጂ የወንጀሉ መፈጸምና ያለመፈጸም ሊጠቀስ የሚገባው ጉዳይ አይደለም፡፡ መንግሥት ግፍ ለሚፈጸምበት አንድ ዜጋውም ቢሆን ተቆርቋሪነትን ማሳየት ግዴታው ነው፡፡ እየሆነ ያለው ግን፣ እጅግ የተለየ ነው፤ ያለፈውን ሁሉ ትተን በወራት ውስጥ የተከሰተውን ሰቆቃ ማሰብ ብቻውን ኢትዮጵያዊነታችንን እንድንጠራጠር አድርጎናል፡፡ ከሰብአዊነት ውጭ የሆነው ክስተት አብሮ የመኖርንና የመዋለድን ታሪክ የፋቀ መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ ለመሆኑ ይህ ሁሉ ሲሆን መንግሥት ምን እያደረገ ነው? በቃል ከመናገር የዘለለ የሕግ የበላይነትን የማስጠበቅ ግዴታውን ሲፈጽ የማይታይ መንግሥትስ ምን ስም ይሰጠዋል?
ይህንን መሠል ግፍና እልቂት አንድ ቦታ ላይ “በቃ!” ማለት ይገባል፡፡ “ሳይርቅ በቅርቡ መመለስ፣ ሳይደርቅ በእርጥቡ ማቃናት” ሲገባ፣ “በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽን” እንደተባለው ተመጣጣኝ ርምጃ ወስዶ ወንጀልን በጅምሩ ማስቆም ሲገባ፤ በቸልተኝነት ማለፍ አሁን ለደርስንበት ቅጥ-ያጣ ሁኔታ እንዳደረሰን መቀበል ግድ ይሆናል፡፡ በወለጋ ይህ ጥቃት የተፈጸመው ዛሬ አይደለም፣ በባሌና በአርሲ፣ በቤኒሻንጉልና በጉራፈርዳ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ዜጎች በዘራቸው የተነሳ ሲጨፈጨፉ ዓመታትን እያስቆጠረ ነው፡፡ እነዚያ ሁሉ ጥቃቶች ግን ይኸ ነው የሚባል ምላሽ አልተሰጣቸውም፡፡ የሕግ የበላይነትም በአግባቡና በትክክለኛው መጠንና ልክ ሲከበርም አላዬንም፡፡
ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ሕዝቡ ተቃውሞአቸውን በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም፣ በርካታ መግለጫዎችን ቢሰጡም፣ መንግሥት ጆሮ መስጠቱን ያመላከቱ ተግባራትን ሲፈጽም አልታየም፡፡ ይህ ጆሮ-ዳባ ልበስ አካሄድም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፎካካሪነታቸው የቃላት መሆኑንና ሃሳባቸው የሚደመጥ ለመሆኑን እንዲገነዘቡና ሕዝብም በለውጡ ላይ ያለው አመኔታ እየቀነሰና እየተሟጠጠ እንዲሄድ ከማድረጉ በስተቀር ያስከተለው ፋይዳ የለም፡፡
ችግሩ በቀጣይነት እየከፋ የሄደባቸው የኦሮሞና የአማራ የፖለቲካ ድርጅቶች አስር ወር ሙሉ ሲሰበሰቡ ቢቆዩም ያመጡት ውጤት የለም፡፡ ይልቁንም በእነዚህ አስር ወራት ውስጥ፣ ሕዝቡ በዘሩ ምክንያት እየተገደለና እየተፈናቀለ፣ ብሎም እየተሰደደ ነው፡፡ በመንግሥት በኩል፣ በሽፍንፍን ለማለፍ የሚቻል ችግር ያለመኖሩን መረዳት የተቻለ አይመስልም፤ ፍርጥርጥ ያለው እውነት እንዲወጣም “አካፋን አካፋ፣ ዶማንም ዶማ” ማለት አልተቻለም፡፡ አንዳንድ የመንግሥት አካላት ችግርን ከማቃለል ይልቅ የችግሩ አካላት፣ የፍጅቱ አራጋቢዎች ሲሆኑ መስተዋላቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ታዲያ ይህ በሆነበት እውነታ መንግሥት በቆራጥነት የሕዝቡን ደህንነት ይጠብቃል ብሎ ለማመን እንዴት ይቻላል? ለመሆኑ ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ሊያመጣ ተስፋ የተጣለበት ለውጥስ “ያሳምራል ያሉት ኩል ዓይን አጠፋ” እንዲሉ ለምን ሆነ?
ኢሕአፓ በተደጋጋሚ ባወጣቸው መግለጫዎች የዜጎችን መጨፍጨፍና መሰደድ ተቃውሟል፡፡ መንግሥት ትክክለኛ ሚናውን እየተጫወተ ሳይሆን በአንዳንድ ሁኔታዎች በሚነደው እሳት ላይ ቤንዚን የመጨመር ክስተቶችን ሊያቆም እንደሚገባና የሕግ የበላይነትን ማስከበር እንደሚገባው አሳስቧል፡፡ ሆኖም ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ሳይሆን እየከፉ መሄዳቸው ይስተዋላል፡፡ የዜጎችን ሰቆቃ እያዳመጡ ትርጉም አልባ ጩኸት መጮህ ይሰለቻል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ውግዘትና ሱባኤ የሕዝብ ጸሎትና ምህላም እነሆ የኢትዮጵያን ስቃይ ለፈውሱ እንዳልቻሉ ተመልክተናል፡፡ እናም እሹሩሩ ሊበቃ ይገባል! ጥፋተኞች ተገቢውን ቅጣት ሊያገኙ፤ ሕዝቡም እፎይ ሊል ያስፈልገዋል፡፡
በትናንትናው ዕለት የተፈፀመው ፍጅት በዓይነቱ ለየት ያለ መሆኑ ታውቋል፤ ሕዝብን ከቤቱ ለስብሰባ አስወጥቶ በቦንብና በጥይት ማጋየቱ፤ ቤትና ንብረት ማቃጠሉ... በርካቶች መግለጫ እንዲያወጡ አድርጓል፡፡ ሆኖም ይህ ቋት አይሞላም፤ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ እልቂቶችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከንግግር ያለፈ ትሩፋት አላመጡም፡፡ ይልቁንስ ሁኔታውን ከስሩ መመርመርና በዓይነቱ ለየት ያለው ዘር-ተኮር ጭፍጨፋ (የዘር-ማጥፋት) እንዲከሰት ያደረገው ሁኔታ ምን እንደ ነበረ እውነተኛውን ምክንያት ማውጣት ያስፈልጋል፡፡ ሕዝብ “ትታችሁን አትሂዱ! ሊጨርሱን ነው!...” ወዘተ እያለ ሲማጸን “ታዝዣለሁ...አልቆይም!” በማለት አካባቢውን የለቀቀው የሀገር መከለካከያ ሠራዊት ሃላፊነቱን መወጣት ለምን አቃተው? ተዕዛዙን ያስተላለፈውስ ማነው? የመከላከያ ሠራዊቱን እግር ተከትሎ የታጣቂው ሃይል ህዝብን ስብሰባ ጠርቶ የመፍጀት ግጥምጥሞሹስ እንዴት ሊፈጠር ቻለ? የቦንብና የመሳሪያ እሩምታ ሲወርድና የሕዝብ ሰቆቃ አየሩን ሲሞላው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል ለምን አልሰማም? የትስ ሄዶ ነበር? .... ለሚሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ በመፈለግ እውነተኛ ፍርድ መስጠት እና የሕግ የበላይነትን ለዘሌቄታው ለማስከበር ይቻል ዘንድ የማያወላዳ ውሳኔ መስጠት ያስፈልጋል፡፡
ኢሕአፓ ይህ የግፍ ተግባር በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል የሚል ጽኑ አቋም አለው፡፡ ወንጀለኞችም ታድነው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥሪውን ያስተላልፋል። ሀገራችን ኢትዮጵያም አሁን ከምትገኝበት አስከፊ የጸጥታ ሁኔታ ወደተሻለና ወደተረጋጋ ሁኔታ እንድትመጣና ሰላም እንዲሰፍን ኢሕአፓ የሚከተሉትን ሰባት ነጥቦች ወይም የመፍትሔ ሃሳቦች ያቀርባል።
- ኢሕአፓበሥልጣንላይያለውመንግሥትከምንጊዜውምየጠነከረናየሕዝብወገናዊነቱንየሚያስመሰክርአስቸኳይእርምጃእንዲወስድያሳስባል፡፡መንግሥትያለምንምማወላወልየሕግየበላይነትንእንዲያረጋግጥናበወንጀለኞችላይያለማመንታትእርምጃእንዲወስድበአንክሮያሳስባል፡፡
- ጽንፍበረገጠየዘረኝነትአመለካከትእናጥላቻየተነሳለተሰዉኢትዮጵያንመንግሥትየሀዘንቀንእንዲሰይምምኢሕአፓይጠይቃል፡፡በሀገራችንውስጥሰላምእንዳይሰፍን፣ኢትዮጵያንደካማሀገርእንድትሆንያላሰለሰሚናበሚጫወተውሕወሃትመራሹኃይልላይምየማያዳግምእርምጃእንዲወሰድእንጠይቃለን፡፡
- በመንግሥትመዋቅርውስጥየተሰገሰጉናየአንድንብሔርየበላይነትመልሰውለማስፈንየሚጥሩአክራሪ “የተረኝነትስሜት” ከተጠናወታቸውብሔርተኞችራሱንእንዲያጸዳእያሳሰብን፤ከዚህቀደምእንደሚደረገውበሕግማስከበርሥርዓትናሂደትበማሳበብአጥፊዎችምንምሳይደርስባቸውለዓመታትናለወራትየዘለቀየፍትሕመጓተትበፍጹምሊኖርእንደማይገባኢሕአፓለመግለጽይገደዳል፡፡
- የኢትዮጵያሁኔታእንዲህከድጡወደማጡእያሽቆለቆለእናወደየትኛውምየኢትዮጵያክፍልመንቀሳቀስአስጊበሆነበትወቅት፣የሰላምእጦትአንገብጋቢበሆነበትነባራዊሁኔታላይ፣አገራዊምርጫየሚደረግበትንምህዳርማሰብእጅግከባድበመሆኑሊታሰብበትእንደሚገባበአንክሮይገልፃል፡፡
- በሀገራችንውስጥለተከሰቱትበርካታችግሮችምንጩናመሠረቱበሥራላይያለውሕገ-መንግሥትበመሆኑበአጭርጊዜውስጥ፣ሕዝቡንያሳተፈየሕገ-መንግሥትጉባዔበመጥራትመሠረታዊማሻሻያእንዲደረግበድጋሚጥሪያችንንእናስተላልፋለን፡፡
- የሀገራችንንምስቅልቅልችግሮችፈርለማስያዝናዘላቂሰላምንእውንለማድረግባለድርሻዎችንየሚያሳትፍሃገራዊውይይትበአስቸኳይእንዲጠራናየብሄራዊመግባባትሂደትምእውንእንዲሆንአበክረንእንጠይቃለን።
- መንግሥትአስቸኳይእርምጃየማይወስድእናጉዳዩንበማለባበስለማለፍየሚሞክርከሆነለኢትዮጵያሕዝብቆመናልየሚሉተፎካካሪየፖለቲካፓርቲዎችለሀገራችንየመንግሥትንያህልሃላፊነትያለብንመሆኑንበመገንዘብግዴታችንንለመወጣትመምከርናየጋራጠንካራሕብረ-ኃይልማቋቋምእንዳለብንኢሕአፓያሳስባል፡፡
በመጨረሻም፣ በዚህ አጋጣሚ፣ በተደጋጋሚ የአብረንእንሥራመልዕክታችንንኢትዮጵያእንደአገርመኖርናመቀጠልእንዳለባትከሚያምኑአገርወዳድኃይሎችጋርበመሆን፣አክራሪብሔርተኞችንመታገልየሚችልጠንካራኃይል (የጋራንቅናቄወይንምመድረክ) መመሥረትአስፈላጊነቱንናወቅታዊነቱንበማመን ጥረቱንም በመጀመር ሀገርና ሕዝብን በጋራ እንድንታደግ ኢሕአፓ ጥሪውን ያቀርባል።
ኢትዮጵያአንድነቷተከብሮለዘላለምትኑር!
ኢሕአፓለተሻለነገ!
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም…. አዲስአበባ!

