SKIP TO MAIN CONTENT

የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል በውስን ሰው እንዲከበር መወሰናቸውን አባገዳዎቹ ገለፁ

*** የኢሬቻ በዓል ከፖለቲካ በጸዳ መንገድ እንዲከበር ጥሪ ቀረበ

Erecha
Source: PD

1 min read

Published

By Stringer


Skip to article content

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና የወቅቱ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል በውስን ሰው እንዲከበር መወሰናቸውን የኦሮሞ አባገዳዎች  ህብረት ገለጸ፡፡

ህብረቱ በሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ክብረ በዓል አከባበር በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

አባገዳዎቹ በመግለጫቸው እንዳሉት በዓሉ በውስን ሰው እንዲከበር ያስፈለገበት ምክንያት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የበለጠ እንዳይስፋፋ እና የወቅቱ የጸጥታ ሁኔታ በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡

ህብረተሰቡም እራሱን እና ቤተሰቡን ከኮቪድ 19 በመጠበቅ በአባ ገዳዎች ህብረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በዓሉን እንዲያከብር አባገዳዎቹ አሳስበዋል፡፡

የኢሬቻ በዓል የሰላም ፣ የፍቅር እና የምስጋና በዓል ነው ያሉት አባ ገዳዎቹ ፣መላው የኦሮሞ ወጣት በዓሉን ከፖለቲካ በጸዳ መንገድ እንዲያከብር ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከአዲስ አበበ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

- ኢቴ


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now