አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኢትዮጵያ መንግሥት 7 የተመድ ሠራተኞችን ከአገር እንዲወጡ ማዘዙ "አስደንግጦኛል" አሉ

*** ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግሥት በተመድ ሠራተኞች ላይ የወሰነውን ውሳኔ እንዲቀለብስ ጥሪ አቀረበች፤ "ለአፀፋ ምላሽ" እንደማታመነታ አስታወቀች

Antonio Guterres, Secretary-General of the United Nations.

Antonio Guterres, Secretary-General of the United Nations. Source: Getty

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰባት የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች በ72 ሰዓታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቅቀው እንዲወጡ ማዘዙ ያስደነገጣቸው መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሴፕቴምበር 30 ባወጡት መግለጫ አስታወቁ። 

ዋና ፀሐፊው "የተመድ ሰብዓዊ ግልጋሎት የሚመራው ዋነኛ መርሆዎቹ በሆኑት ሰብዓዊነት፣ አለማዳላት፣ ገለልተኛነትና ራስ አደርነት" እንደሆኑ ጠቅሰዋል። 

አያይዘውም፤ ተመድ ኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ፣ መድኃኒት፣ ውኃና የመፀዳጃ አቅርቦቶችን የመሳሰሉ ሕይወት አድን ረድኤቶችን ለችግረኞች ማቅርቡን አመላክተው የተመድ ጠቃሚ ሥራ እንዲቀጥል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ብልሃት ለማፈላለግ በመነጋገር ላይ መሆኑን ገልጠዋል።  

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰባቱን የተመድ ሠራተኞች በ72 ሰዓታት ከአገር እንዲወጡ ያዘዘው "በአገር ውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብተዋል" በሚል አስባብ ነው። 

ባለፈው ኦገስት የኢትዮጵያ መንግሥት የዳች ቅርንጫፍ የሕክምና ረድኤት ድርጅት ድንበር አልባ ሐኪሞችንና የኖርዌጂያን ስደተኞች ምክር ቤትን "አማፂያን ቡድናት በማስታጠቅ" በሚል ከእአገር እንዲወጡ መወሰኑ ይታወሳል። 

ይህ በእንዲህ እንዳለም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግሥት ሰባቱን የተመድ ሠራተኞች ከአገር እንዲወጡ የወሰነውን ውሳኔ እንደምትቃወም ገልጠዋል።

አክለውም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት "ውሳኔውን እንዲቀለብስ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ ታቀርባለች፤ ለአፀፋ ምላሽም አታመነታም" ብለዋል።


1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now