SKIP TO MAIN CONTENT

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በስልክ ተነጋገሩ

*** የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የውስጥ ወሰኖችንም ሆነ ዓለም አቀፍ ድንበር በኃይል ወይም ሕገ መንግሥቱን በመጣስ መለወጥ እንደሌለበት ማንሳታቸውን ገለጡ

Abiy Ahmed, Ethiopia's prime minister.
U.S. Secretary of State Antony Blinken (L) and Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed (R). Source: Getty

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ጁላይ 6 ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።

አቶ ብሊንከን በግጭት ላይ ባሉ ሁሉም ወገኖች ዘንድ አስቸኳይና ዘላቂ ተኩስ የማቆሙን አስፈላጊነት አንስተው ማሳሰባቸውንና የተከዜ ድልድይ መፍረስንም አስመልክቶ ማውገዛቸውን ጠቅሰዋል። 

አያይዘውም፤

  • የኤርትራ ጦርና የአማራ ሚሊሺያ ከትግራይ ሙሉ በሙሉ ለቅቀው እንዲወጡ
  • ሰብዓዊ እርዳታን ለሚሹ ረድኤት ለመድረስ ሙሉ ተደራሽነት እንዲኖር
  • በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂ በሆኑት ላይ ግልፅ የሆነ ሂደት እንዲዘረጋ
  • የኢትዮጵያን የውስጥ ወሰኖችንም ሆነ ዓለም አቀፍ ድንበር በኃይል ወይም ሕገ መንግሥቱን በመጣስ መለወጥ እንደሌለበት
  • ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፍኖ ያለውን የጎሳና ፖለቲካ ክፍፍሎች ሁሉን አቀፍ በሆነ ዘላቂ መፍትሔ የሚያስገኝ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲካሔድ በተባበሩት መንግሥታት ፀጥታ ምክር ቤት የተመከረበትን ግብር ላይ እንሲያውሉ ያበረታቱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የስልክ ንግግሩን አስመልክቶ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now