SKIP TO MAIN CONTENT

የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ አበባ ለሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ማሳሰቢያ ሰጠ

*** የኤምባሲው ድርጊት የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የሚጎዳ እንደሆነም ተመልክቷል

SBS Amharic
Source: SBS Amharic

1 min read

Published

By Stringer Report


Skip to article content

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ የአሜሪካ ኤምባሲና ድርጅቶች የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨት መቀጠላቸውን ጠቅሰው ከድርጊታቸውም እንዲቆጠቡ ኣሳስበዋል።

ሚኒስትር ደኤታው ‘ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ተከባለች’ የሚል መረጃን ያሰራጩ እንደነበር አውስተው፤ አሁን ደግሞ ‘ሽብር ይፈፀማል’ የሚል የሃሰት መረጃዎችን ያስራጫሉ ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፤ ኤምባሲው ከራሱ አልፎ ሌሎች ኤምባሲዎችንና ተቋማትን እንዲወጡ ጫና እያሳደረ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰሙ ሲሆን፤ ድርጊቱ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የሚጎዳ መሆኑንም አመላክተዋል።

ፋና እንደዘገበው ‘የአሜሪካ እርዳታ ድርጅቶች እርዳታ ትተን እንወጣለን’ የሚል ማስፈራሪያ ማንሳታቸው ይሰማል ያሉት አቶ ከበደ፤ 'ኢትዮጵያውያን ክብራችን በስንዴ አንለውጥም' ብለዋል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now