የኢትዮጵያ አየር መንገድ በይፋዊ ገፁ እንዳስታወቀው "በአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ" ዘርፍ ለተከታታይ አራት ዓመታት ፣ "በአፍሪካ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ" ዘርፍ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት፣ "በአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ" ዘርፍ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት እንዲሁም "በአፍሪካ ምርጥ የበረራ መስተንግዶ ሰራተኞች" ዘርፍ አንደኛ ለመሆን ችሏል።
አየር መንገዱ በSKYTRAX ምርጥ የዓለም 100 አየር መንገዶች ዝርዝር ውስጥም በ37 ኛ ደረጃ ለመቀመጥ የቻለ ሲሆን ውድድሩ በዓለማችን ላይ ከሚገኙ 350 በላይ አየር መንገዶችን ያሳተፈ መሆኑ ተገልጿል።
[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ]

