የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ የጭነት አውሮፕላንነት የቀየራቸውን የመንገደኛ አውሮፕላኖቹን መልሶ ወደ ቀድሞ ግልጋሎታቸው እያሰማራ ነው

*** እሥራኤል የቦይንግ መንገደኛ አውሮፕላንን ወደ ጭነት አውሮፕላን የሚቀይር ማዕከል አዲስ አበባ ላይ ልታቆም ነው

Ethiopian Airlines Airbus 350-900.

Ethiopian Airlines Airbus 350-900. Source: Getty

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ወደ ጭነት አውሮፕላንነት ቀይሯቸው የነበሩ አውሮፕላኖችን መልሶ ለመንገደኞች ማጓጓዣ ግልጋሎት ማዋል ጀመረ። 

አየር መንገዱ ከመንገደኛ ማጓጓዣነት ወደ ጭነት አጓጓዥነት ቀይሯቸው የነበሩ አራት ቦይንግ 777-200 የቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችንና ክትባቶችን ከቻይና ወደ አፍሪካና ብራዚል አጓጉዞባቸዋል። 

ይሁንና በአሁኑ ወቅት የመንገደኞች አውሮፕላን ግልጋሎት እየጨመረ በመምጣቱ ሶስቱ ተመልሰው ወደ ቀድሞ ግልጋሎት ሰጪነታቸው የዞሩ ሲሆን አራተኛውም ከጭነት ወደ መንገደኛ አውሮፕላንነት እየዞረ መሆኑ ተነግሯል።

በሌላም በኩል የእሥራኤል መንግሥት ንብረት የሆነው የእሥራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪዎች ባለፈው ሐሙስ እንዳስታወቀው የቦይንግ መንገደኛ አውሮፕላንን ወደ ጭነት አውሮፕላንነት ቀያሪ ተቋሙን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚያቋቋም ገልጧል።

.
Ethiopian Airlines Boeing 777F Cargo Aircraft. Source: Getty

ኩባንያው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ባካሄደው ስምምነት መሠረት ከመንገደኛ ወደ ጭነት የመለወጫ ማዕከሉን አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው የአየር መንገዱ የጥገና ማዕከል ውስጥ የሚያደርግ ይሆናል። 

 


1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now