SKIP TO MAIN CONTENT

በአየር ጠባይ ጫና ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ማረፊያዎች ተዛወሩ

*** "ከብዙ ጥንቃቄዎች ጋር ወደ አዲስ አበባ የሚያቀኑ በረራዎች ወደ ቅርብ አየር ማረፊያዎች እንዲዛወሩ አድርገናል" የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Ethiopian Airlines Airbus 350-900
Ethiopian Airlines Airbus 350-900. Source: Getty

1 min read

Published

By Demeke Kebede


Skip to article content

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በክረምቱ ጭጋጋማ አየር የተነሳ የበረራዎች ማረፊያን በቅርብ ወደ ሚገኙ አየር ማረፊያዎች ማዛወሩን ገልጿል።

ዛሬ በሶልሻሚዲያ ገፆቹ ይፋ ባደረገው መግለጫው ክረምቱ በመክበዱ ትናንት ለተፈጠሩ መስተጓጎሎች ይቅርታ ጠይቋል።

በአዲስ አበባና ዙሪያው ባለው ከፍተኛ ደመና የተነሳም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደረጉ የነበሩ በረራዎችን ማረፊያ ወደ ቅርብ ማረፊያዎች ማዛወሩን ገልጿል፡፡ "ከብዙ ጥንቃቄዎች ጋር ወደ አዲስ አበባ የሚያቀኑ በረራዎች ወደ ቅርብ አየር ማረፊያዎች እንዲዛወሩ አድርገናል" ብሏል፡፡

"ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ስለሆነ ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አሁን በአማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች እያረፉ፤ የአየር ሁኔታው ሲሻሻል ወደነበረበት ይመለሳሉ" ያለው አየር መንገዱ “ከቁጥጥራችን በላይ በሆነ ምክንያት ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን” ብሏል። ስለ በረራዎቹ ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ለደንበኞቹ በየጊዜው እንደሚገልፅም አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባና ዙሪያው በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ጭጋግ የሚስተዋልበት ከተማ በመሆኑ ለትራፊክ ፍሰት እንኳን አስቸጋሪ መሆኑን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው።

በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጄንሲን ሃሳብ ለማካተት ያደረኩት ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ [


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now