የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አቪየሽን ታሪክ የመጀመሪያ የሚሰኝ የአውሮፕላን ጥገና አደረገ

*** የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Ethiopian

Source: Supplied

የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅን እና የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ /winglet modification/ አደርገዋል ሲል አይዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ማሻሻያው በቦይንግ 767 አውሮፕላኖች ላይ የተደረገ ነው ያለው አየር መንገዱ በአፍሪካ አቪየሽን ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል ነው ብሏል፡፡

በአመት እስከ 500 ሺህ ጋሎን ነዳጅ ለመቆጠብ እና 277 ሺህ ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀትን እንደሚያስቀርም ነው የገለጸው፡፡

ይህ አየር መንገዱ በአካባቢ ጥበቃ የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ያለም ሲሆን የማሻሻያ ፕሮጄክቱ በ69 የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች ጥረት መሳካቱን አስታውቋል፡፡


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now