የሕዝባችን ዕምባ መድረቅ አለበት!

ከኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን የሰላምና የትብብር አድቮካሲ ግሩፕ - በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

Ethiopian - Australian Peace and Solidarity Advocacy Group

Source: SBS Amharic

የኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን የሰላምና የትብብር አድቮካሲ ግሩፕ ፤ ኢትዮጵያ  ላይ የደረሰው የሰሞኑ ሰቆቃ በእጅጉ ያሳሰበን በመሆኑ ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል።

በአገራችን በተለይም በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ሁለገብ አስቃቂ ጥፋት በእጅጉ እንዳሳዘነን እየገለጽን ጽንፈኞች ባስነሱት በዚህ ሁከት ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

የሕዝባችን ዕምባ መድረቅ አለበት። ውስጣችን ተሸጉጠው የሚቦረቡሩን ባንዳዎች ሌላ ጥፋት ከመሰነቃቸው በፊት ሊመነጠሩ ይገባል።  የውጭ ጠላቶቻችንን መግቢያ ቀዳደዎች ሁሉ መድፈን መቻል አለብን።
የሕዝባችን ዕምባ መድረቅ አለበት
እርግጥ ነው መንግሥት የተለያዩ ግዙፍና አቻ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችና ተግዳሮቶች እንደገጠሙት በሚገባ እንረዳለን። ይሁን እንጂ የተለያዩ የፍትህና የጸጥታ አካላት ይህንን እኩይ ተግባር  ቀድመው ማክሸፍ ይጠበቅባቸው ነበር።  «ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ እንዲሉ» በቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በብቃት ባለመሰራቱ ሕዝባችንና አገራችንን ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሏል።

ከዚህ በፊት ከተከሰቱ ተመሳሳይ ችግሮችም ጋር በተያያዘ ትኩረት መሻት የሚገባቸው ቀጠናዎች ተለይተው ስለሚታወቁ  በእነዚህ አካባቢዎች ልዩ ትኩረት ማድረግ ቀዳሚ ሥራ መሆን እንደነበረበት ይታመናል። ይህ አሳዛኝ ክስተት ለመንግሥት የመጨረሻው የማንቂያ ደወል ሆኖ ዳግም መሰል ሁኔታ እንዳይከሰት  መሰረታዊ ሥራ መስራት የሚጠበቅበት ጊዜ እንደሚሆን እንተማመናለን።

የኢትዮጵያ ሕልውና የሁሉም ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ጽንፈኞችን፤ ዘረኞችን በማይመቻቸው መንገድ ሥርዓት የማስያዙ ጉዳይ የመንግሥት ኃላፊነት መሆኑ ላፍታም ሊዘነጋ አይገባም።

በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሕዝብን የጨፈጨፉ ግለሰቦች፤ የተባበሩ የጸጥታ አካላት ተባባሪ ባለስልጣኖች ጥፋታቸው ትንሽ ትልቅ ሳይባል ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እያሳሰብን፦ከሁሉም በላይ የዚህ ሁሉ ጥፋት መሰረቱ  የዘር ፓለቲካና በወጣቱ ላይ የተነዛው የዘር ጥላቻ  በመሆኑ በሕዝብ መካከል እየተቆፈረ ያለው የልዩነት ሸለቆ ከፍተኛ ነው።

ስለሆነም ይህንን አመለካከት የሚቀለብስና ብሎም የሚያከስም በሥልት የታገዘ የአመለካከት ለውጥ ስራ በወጣቱ ዘንድ በመንግሥት በኩል ትኩረት እንዲሰጠው  ሳናሳስብ አናልፍም።

በተለያየ መገናኛ ብዙሃን በማህበራዊ ሚዲያና በመሳሰሉት ጥላቻና ክፍፍል በሕዝባችን መካከል የሚነዙትን በጥብቅ እያወገዝን ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በጽኑ እናሳስባለን።

ለኢትዮጵያ ህልውና ሲባል መንግሥት በሚያደርገው አገር አድን እንቅስቃሴ ላይ በቁርጠኝነት ተባባሪ እንደምንሆንም በዚህ አጋጣሚ  እንገልጻለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን የሰላምና የትብብር አድቮካሲ ግሩፕ


Share

2 min read

Published

Updated



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service