SKIP TO MAIN CONTENT

“በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፡ ፀጥታና ደኅንነትን ለማጠናከር ፈጣንና የተቀናጀ እርምጃ አስፈላጊ ነው" - ኢሰመኮ

*** የሚገመተው የተጎጂዎች ቁጥር 34 ቢሆንም ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል።

EHRC
Chief Commissioner of Ethiopian Human Rights Commission Source: PD

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

" የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኅዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ሌሊቱን፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በደባጤ ወረዳ ከወንበራ ወደ ቻግኒ በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላሻ አውቶብስ ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት የተሰማውን ኃዘን” ኅዳር 6 ባወጣው መግለጫ ገልጧል።።

 ኢሰመኮ በደረሰው መረጃ መሰረት በተመሳሳይ ወቅት በሌሎች የክልሉ ወረዳዎች (ውብጊሽ፣ያምፕ እና ቂዶህ) ጥቃት መሰንዘሩ እና ለጊዜው ሕይወታቸውን ለማዳን የሸሹ ሰዎች መኖራቸው በመነገሩ፣ በአሁኑ ወቅት  የሚገመተው የተጎጂዎች ቁጥር 34 ቢሆንም ሊጨምር እንደሚችል  ይጠበቃል።

 የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ይህ ጥቃት ሁላችንም በጋራ የተሸከምነውን የሰው ሕይወት ክፍያ ዛሬም በአሳዛኝ ሁኔታ የሚያሻቅብ ነው። የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በፍጥነት ጥቃቱ የበለጠ እንዳይባባስ እርምጃ መውሰዳቸው  አበረታች ነው” ብለዋል።

መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ኢሰመኮ ያወጣውንና በክልሉ የሚከሰቱ ጥቃቶች ተደጋጋሚነትና አስከፊ ባሕሪይ በተለየ ሁኔታ ያሰመረበትን መግለጫ በማስታወስ፣ ዋና ኮሚሽነሩ የሚከተለውን አክለዋል፤

“በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ፋታ የማይሰጥ ሆኖ በመቀጠሉ፤ በፌዴራልና በክልሉ መንግሥታት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በፍጥነትና ንቁ ሆኖ መጠበቅ ላይ የተመሰረተ የተሻለ ቅንጅት የሚሻ ነው። የፌዴራልና የክልሉ የፀጥታና የፍትሕ አካላት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እነዚህን ጥቃቶች  ሊያስቆም የሚችል አዲስ ክልላዊ የፀጥታ ስትራቴጂ  ሊነድፉ ይገባል።”


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now