ኢሰመኮ ጋምቤላ ከተማ ውስጥ በተቋሙና ሠራተኞቹ ላይ የተቃጣው ጥቃት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ላይ ብርቱ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር አሳሰበ

ኢሰመኮ በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች ጋምቤላ በሚገኘው ጽሕፈት ቤቱ ዘልቀው የተለያዩ የጥፋት ድርጊቶችን እንደፈጸሙ፣ በባልደረቦች ላይ ዛቻ፣ የሰብዓዊ መብቶች ሥራዎችን የሚያከናውኑ ድርጅቶችም “ከከተማው ለቅቀው እንዲወጡ” ማስፈራሪያ የደረሰባቸው መሆኑን በማመልከት ድርጊቶቹ እንዲገቱ ጠይቋል።

Dr Daniel Bekele.jpg

Dr Daniel Bekele, Chief Commissioner of the Ethiopia Human Rights Commission (EHRC). Credit: PR

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የፌዴራል ፖሊስ የምዕራብ መምሪያ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ለኮሚሽኑ በሰጠው ምላሽ በሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ኦነግ ሸኔ እና ጋነግ ታጣቂዎች በከፈቱት ውጊያ ከመንግሥት በኩል “የፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ልዩ ኃይሎች እና መደበኛ ፖሊሶች መሳተፋቸውን” እንደተገለጠለት አመልክቷል።

አያይዞም “በውጊያው ወቅት በተወሰነ መልኩ የሰው እንቅስቃሴ በከተማ ውስጥ ስለነበር፤ በበራሪ ጥይቶች የተመቱ ሲቪል ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ” ግምት የነበራቸው ቢሆንም፣ “ከውጊያው በኋላ ባደረጉት ማጣራት የክልሉ ልዩ ኃይሎች በተለይ ሰኔ 8 እና 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በከተማው በሲቪል ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳደረሱ መረዳታቸውን” አስፍሯል።



የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ ላይ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በጋምቤላ ክልል የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖቹ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አስመልክቶ ያከናወነውን የምርመራ ሪፖርት መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በሪፖርቱ በዝርዝር እንደተመለከተው ከሰኔ 7 እስከ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲቪል ሰዎች ላይ የደረሱትን ጉዳቶች አስመልክቶ ኮሚሽኑ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ፣ ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት፣ ከፌዴራል ፖሊስ የምዕራብ መምሪያ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ሬጅመንት፣ ከከተማው ማዘጋጃ ቤት እና ከጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል ስለ ጉዳዩ መረጃ እና ምላሽ መቀበሉ ሰፍሯል።

ሆኖም የሪፖርቱን ይፋ መደረግ ተከትሎ በማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾች እና መገናኛ ብዙኃን የተሳሳተ፣ አነሳሽ እና ዛቻ ያዘሉ መረጃዎች ሲሰራጩ፤ እንዲሁም በኢሰመኮ ባልደረቦች ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ መልእክቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። ኮሚሽኑ ጉዳዩን ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍታት እንደሚቻል በማመን ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቦ መቆየቱም ተገልጧል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም፤ መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በቡድን ሆነው የመጡ ሰዎች ወደ ኢሰመኮ ጋምቤላ ጽሕፈት ቤት በመሄድ የተለያዩ የጥፋት ድርጊቶችን የፈጸሙ ሲሆን፣ በኢሰመኮ ባልደረቦች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ አድርሰዋል። እንዲሁም በከተማዋ የተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ሥራዎችን በሚያከናውኑ ሌሎች ድርጅቶች ላይ ተመሳሳይ ጥፋት አድርሰው ድርጅቶቹ “ከከተማው ለቅቀው እንዲወጡ” ማስፈራራታቸውንም ገልጧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኮሚሽኑ በሕገ መንግሥት የተቋቋመ ፌዴራል የብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋም መሆኑንና የኮሚሽኑ ሠራተኞችም በአዋጅ የልዩ መብት ጥበቃ የሚደረግላቸው መሆኑን አስታውሰው፣ “ኮሚሽኑ የክትትል እና የምርመራ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት የተለያዩ ተግዳሮቶች የሚገጥሙት ቢሆንም፤ ይህንን ዐይነት በብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋም እና ሠራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና በክልሉ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ምልከታ የሚጥል በመሆኑ የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት ተባብረው በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ ኮሚሽኑ በጥብቅ ያሳስባል” ብለዋል።

ከሰኔ 7 እስከ ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጎጂዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች አሁንም ሟቾች የተቀበሩበትን ቦታ ለማወቅ እና ፍትሕ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ በመሆናቸው የኮሚሽኑ ምክረ ሃሳቦች በአፋጣኝ እንዲተገበሩ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በድጋሚ አስታውሰዋል።

Share

Published

Updated

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service