"መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር" - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

*** በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የግፍና የጭካኔ ወንጀሎች መደጋገም፣ የችግሩን ስር መሰረት ለመፍታት የሚያስችል የተሟላ ብሔራዊ የግፍና ጭካኔ ወንጀል መከላከያ ስትራቴጂ ነድፎ በአፋጣኝ በስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ ኢሰመኮ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።

EHRC

Dr Daniel Bekele, Chief Commissioner of Ethiopian Human Rights Commission (C) Source: SBS Amharic

"መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር" በሚል ርዕስ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ የተከሰቱ የሰብአዊ ጉዳቶችን የምርመራ ዋና ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

በጋዜጣዊ መግለጫ ለተገኘን ጋዜጠኞች የኮሚሽኑ ኃላፊዎች እንደገለፁንል፤

~ ከሰኔ 22-24/2012 በነበሩት ሶስት ቀናት በተፈፀመው ጥቃት 123 ሰዎች ሲሞቱ በ500 ሰዎች ላይ ደግሞ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

~ ምርመራው የተከናወነው በ40 የኦሮሚያ አካባቢዎች ብቻ ሲሆን ያልተካተቱ ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገልጿል።

~ ጥቃቱን የፈፀሙ ሰዎችና ቡድኖች ያደረሷቸው ጥቃቶች "በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል : Crime against humanity"  ባሕርያትን የሚያሟሉ ናቸው።

~ በዚህ መጠነ ሰፊ ጥቃት የተሳተፉት ብዙ ቁጥር ያላቸው እና ከቦታ ቦታ በቡድን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ወጣቶች ናቸው

~ ጥቃቱም የተፈፀመውም በጩቤ፣ በድንጋይ፣ በእሳት፣ በኤሌክትሪክ ገመድ፣ በዱላ፣ በዶማ፣ በገጀራ እና በመጥረቢያ ተጠቅመው ነው።

~ ጥቃቱ ፍጹም ግፍና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በማሰቃየት እና በማረድ ጭምር ሰዎችን የመግደል ድርጊት ነው።

~ በአብዛኛው በቡድን የተደራጁ ሰዎች ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ፣ በብሔርና በሃይማኖታቸው ተለይተው በተለይም አማራዎችን እንዲሁም የኦርቶዶክስ አማኝና ሲቪል ሰዎችን፣ ቢያንስ በ40 የተለያዩ ቦታዎች በተስፋፋና ለሦስት ቀናት በቆየ ሁከት አጥቅተዋል።

~ በአንዳንድ ቦታዎች ድረሱልን ለሚሉ ተጠቂዎች የፀጥታ አካላት ቸልታ ማሳየታቸው ወይም ከበላይ አካል አልታዘንንም ማለታቸው ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል።

~ ምንም እንኳን የፀጥታ ኃይሉ በየቦታው የገጠመውን መጠነ ሰፊ የፀጥታ መደፍረስ ችግር እና የፀጥታ አባሎቹንም የሕይወት መስዋዕትነት በሚጠይቅ ሁኔታ በመሰማራታቸው ኃላፊነታቸው እጅግ ፈታኝ ነበር።

~ በተወሰኑ ቦታዎች ደግሞ የኃይል አጠቃቀም ተመጣጣኝነት ከፍተኛ ጥያቄ የሚያስነሳሆኗል።

~ በአንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው ያልተመጣጠነ እርምጃ፣ ሰልፍ ውስጥ ያልነበሩ በመንገድ ወይም በቤታቸው በር ላይ የተገደሉ፣ ለማሸማገል ጣልቃ የገቡ የአገር ሽማግሌዎችን እና የአዕምሮ ህመምተኛ ጭምር እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል።

~ ተጎጂዎች የነበረውን ሁኔታ " መንግስት ያለ አይመስልም ነበር" ሲሉ ገልፀውታል።

~ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የግፍና የጭካኔ ወንጀሎች መደጋገም፣ የችግሩን ስር መሰረት ለመፍታት የሚያስችል የተሟላ ብሔራዊ የግፍና ጭካኔ ወንጀል መከላከያ ስትራቴጂ ነድፎ በአፋጣኝ በስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ ኮሚሽኑ መክሯል።

~ በሰው ኃይል ማነስ፣ ከችግሩ ስፋት የተመጣጠነ በጥልቀት ለመመርመር በማሰብና ተደራራቢ ችግሮች መበራከት ሪፖርቱን በፍጥነት አጠናቅሮ ለማቅረብ ምክንያቶች እንደነበሩና ስድስት ወራት እንደፈጀ ተገልጿል።

 


2 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now