“በቤንሻንጉል ጉሙዝ በንጹኃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ እጅግ አሳስቦኛል” - ኢሰመጉ

*** የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)

Benishangul-Gumuz

Survivors Of Benishangul-Gumuz Attack. Source: Getty

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ  መንግሥት፣ መተከል ዞን፣ በቡለን፣ ድባጤ፣ እና ዳንጉር ወረዳዎች ላይ በንጹኃን ሰዎች  ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ እጅግ አሳስቦኛል አለ

 ትናንት ማምሻውን ባወጣው ሪፓርትም፦

 - ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም  ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ የሚሄድ መኪና ውስጥ የነበሩ ተጓዦች ማንዱራ ከተማ ላይ  በታጣቂዎች እንዲወርዱ ተደርጎ አንድ ሰው መገደሉን እና ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን፤

 - ከጥር 2 - 3 ቀን 2013 ዓ.ም በቡለን እና ጉባ  ወረዳዎች፣ ኦሜድላ እና አይነሸምስ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት  ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና መኖሪያ ቤቶችም መቃጠላቸውን አካቷል።

 አንድ የዓይን እማኝም ‹‹በድባጤ ወረዳ፣ ቆርቃ ቀበሌ፣ ዳሌቲ በተባለች መንደር ትላንት ጥር  4 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ የኦነግ ሸኔ እና የቤኒን ታጣቂዎች በፈጸሙት  ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን፣ እስከአሁን ድረስ እኔ ራሴ ባለሁበት የ82 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ መገኘቱን እና የቀብር ቦታዎች እየተዘጋጁ መሆኑን አይቻለሁ›› ሲሉ መግለጻቸውን ጠቅሷል።

 ኢሰመጉ በትላንትናው ዕለት ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ከ100 ሊበልጥ እንደሚችልና በአብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውን ጠቅሷል።


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now